ኢትዮጵያዊዉ ታዋቂ ጠበቃ ተከሰሱ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 3 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነትና በተያያዥ ወንጀሎች ለከሠሠና በጥርጣሬ ላሠራቸዉ የሐይማኖት መሪዎች፤ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ነፃ ጋዜጠኞች ጥብቅና ቆመዉ የሚከራከሩት የሕግ ባለሙያ አቶ ተማም አባ ቡልጉ ተከሰሰ።ጠበቃ ተማም የተከሰሱት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚባለዉ የመንግሥት መገናኛ ዘዴ ሥለተከሳሾች ያቀረበዉን ዘገባና የፀረ-ሽብር ሕጉን በመተቸታቸዉ ነዉ።አቶ ተማም በፍትሕ ሚኒስቴር የፌደራል ጠበቆች የሥነ-ሥርዓትና ዲስፒሊን ጉባኤ ፊት ቀርበዉ ነበር።ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ