1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዊዉ የቦን ዩንቨርስቲ ተማሪና ተሞክሮዉ  

እሑድ፣ ግንቦት 27 2009

የፊታችን ሐምሌ መጀመርያ ላይ በሰሜናዊ ጀርመን በምትገኘዉ የጀርመን የወደብ ከተማ በዓለም የበለፀጉ ሃገራትን የሚያስተናብረዉ የቡድን ሃያ ጉባዔ ላይ የሚቀርብ ጥናታዊ መረጃን ለማሰባሰብ በርካታ የዓለም ሃገራት ምሁራን በተሳተፉበት በቡድን 20 ቅድመ ጉባዔ ላይ የተሳተፈዉ ኢትዮጵያዊ እንዳለዉ አበበ ነዉ።

Endalew Abebe, Student Bonn
ምስል privat

እንዳለዉ አበበ

This browser does not support the audio element.


እንዳለዉ በዚሁ የራድዮ ጣቢያችን በሚገኝበት በቦን ከተማ ነዋሪ ከሆነ ዘጠኝ ወር ሞላዉ። እንዳለዉ የጀርመን የአካደሚ ልውውጥ አገልግሎት « DAAD »በሰጠዉ የትምህርት እድል በቦን ዩንቨርስቲ በምድር ወገብ አካባቢ ባሉ ሃገራት ትኩረት የሚያደርግ በግብርና እና የተፈችሮ ሃብት አስተዳደር ላይ የተመሰረተ የሁለተና ዲግሪ ትምህርቱን እየተከታተለ ነዉ። ባለፈዉ ሚያዝያ ወር በርሊን ላይ ለሁለት ቀናት በተካሄደዉ የቡድን 20 ቅድመ ስብሰባና አዉደ-ጥናት ላይም ተካፋይ ነበረ። በቅርቡ ለትምህርታዊ ጉብኝት በሚማርበት በቦን ዩንቨርስቲ በኩል የኢራንን ዋና መዲና ቲህራንንም ጎብኝቶ ነዉ የተመለሰዉ።  እንዳለዉ አበባ በጀርመን የመጀመርያ ወራቶች ቆይታዉንና ስለትምህርቱ በጥቂቱ ጠይቀነዋል። ሙሉዉን ቅንብር ይከታተሉ። 


አዜብ ታደሰ
ልደት አበበ 

እንዳለዉ አበበ

This browser does not support the audio element.

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW