የዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ሐይል ባልደረባ የነበረዉ ዮናታን መላኩ የተያዘዉ በጀርባዉ ባዘለዉ ቦርሳና በመኪናዉ ተቀጣጣይ ፈንጂ አጭቆ አሜሪካዉ መከላከያ ሚንስቴር ሕንፃ አጠገብ ሲዘዋወር ተገኝቷል በሚል ጥርጣሬ ነበር።ተጠርጣሪዉ ፍርድ ቤት የቀረበበት ክስ ግን ያሸባሪነት ሳይሆን የሌብነት ወንጀል ነዉ።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ሁኔታዉን ተከታትሎት ነበር።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ