1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያን ያሸነፉባቸው የዳይመንድ ሊግ ውድድሮች እና የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ፍጻሜ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 13 2016

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል የተጎናጸፉባቸው የዳይመንድ ሊግ እና ሌሎች የአትሌቲክስ ውድድሮች በተለያዩ ሀገራት ተከናውነዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሲጠበቅ የነበረውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ የማራቶን ቡድኑን ይፋ አድርጓል ። ማንችስተር ሲቲ ለአራተኛ ተከታታይ ዓመት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል።

Manchester City gewinnt Premier League | 2024
ምስል Molly Darlington/REUTERS

የግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት

This browser does not support the audio element.

በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የተከናወኑ አበይት ስፖርታዊ ክንዋኔዎች
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል የተጎናጸፉባቸው የዳይመንድ ሊግ እና ሌሎች የአትሌቲክስ ውድድሮች በተለያዩ ሀገራት ተከናውነዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሲጠበቅ የነበረውን  የፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ የማራቶን ቡድኑን ይፋ አድርጓል ። ማንችስተር ሲቲ ለአራተኛ ተከታታይ ዓመት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል። የጀርመን ቡንደስ ሊጋ አሸናፊው ባየር ሊቨርኩሰን አዲስ ታሪክ የጻፈበትን ዓመት አሳልፏል። በጀርመን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የእግር ኳስ ውድድርም በኢትዮ በርሊን አሸናፊነት ተጠናቋል። 


የሞሮኮዋ ማራካሽ ባስተናገደችው የዳይመንድ ሊግ ውድድር በሴቶች የ5 ሺ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊያኑ መዲና ኢሳ እና ፉተን ተስፋዬ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል። በውድድሩ መዲና ኢሳ 14 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ ከ16 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ስታሸንፍ ሌላዋ የሀገሯ ልጅ ፉተን ተስፋዬ በማይክሮ ሰከንዶች ብቻ ተቀድማ  14 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ወጥታለች።

በውድድሩ ኬንያዊቷ ኤዲና ጄቢቶክ ሶስተኛ ወጥታለች። በ800 ሜትር የሩጫ ውድድር የተካፈለችው  ሃብታም ዓለሙ 2ኛ ስትወጣ የገባችበትም ሰዓት 1 ደቂቃ ከ57 ከ70 ማይክሮ ሰከንድ ሆኗል። በተመሳሳይ የውድድር መድረክ በሶስት ሺ ሜትር መሰናክል የተካየኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንጸባራቂ ድል እና የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜፈሉት ጌትነት ዋለ እና ሳሙኤል ፍሬው ሁለተኛ እና አራተኛ በመውጣት ውድድራቸውን አጠናቀዋል። 

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንጸባራቂ ድል እና የአፍሪቃ ዋንጫ ፍጻሜ
ባለፈው ዓርብ እና ቅዳሜ የአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ ባስተናገደችው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ድል ተጎናጽፈዋል። በሴቶች በ1500 ሜ ብርቱ ፉክክር ያደረጉት ድርቤ ወልተጂ እና ፍሬወይኒ ኃይሉ አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን አሸንፈዋል። ድርቤ ርቀቱን 3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ስታሸንፍ አንገት ለአንገት የተናነቀቻት ሌላዋ የሀገሯ ልጅ ፍሬወይኒ ኃይሉ 3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ48 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ሆናለች ። በውድድሩ ኬንያዊቷ ሱዛን ሎካዮ ሶስተኛ ወጥታለች። 
ባለፈው ዓርብ በተደረገው የወንዶች የ5ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር ሰለሞን ባረጋ አሸንፏል። በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ በሪሁ አረጋዊ ሁለተኛ በመሆን ገብቷል። ሰለሞን ባረጋ  ርቀቱን 12 ደቂቃ ከ51ሰከንድ ከ60 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ሲያሸንፍ በሪሁ አረጋዊ አንድ በሰከንድ ብቻ ተቀድሞ 12 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ ከ60 ማይክሮ ሰከንድ የገባበት ሰዓት ሆኗል። በርቀቱ በተደጋጋሚ በማሸነፍ የሚታወቁት ዩጋንዳዊያኑ ጆሹዋ ቼፕቴጌ እና ጃኮብ ኪፕሊሞ ሶስተኛ እና አራተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል። 

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ2024ቱ የፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፈውን የማራቶን ቡድኑን ይፋ አድርጓል። ፌዴሬሽኑ ከረዥም ጊዜ ተጠባቂነት በኋላ ይፋ ባደረገው የቡድን ስብስብ አንጋፋው የኦሎምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮናዎች አሸናፊው ቀነኒሳ በቀለ በወንዶች ብሄራዊ ቡድን ውስጥ መታቀፉን ይፋ አድርጓል። የማራቶን ቡድኑ ይፋ መደረጉን ተከትሎ ምርጫዉ ብዙኃኑን ያስማማ እንደነበር ቢገለጽም አሁንም ግን ከውዝግብ ነጻ መሆን እንዳልቻለ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት ።  በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ማራቶን ብሔራዊ ቡድን ምርጫ እና አንድምታውን በተመለከተ የአዲስ አበባውን ተባባሪ ዘጋቢያችን ምስጋናው ታደሰን ከጥቂት ጊዜ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። 

ሰለሞን ባረጋ የሎስ አንጀለስ የ500 ሺ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድርን አሸነፈምስል DW/H.Tiruneh

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቦስተን ድል ቀንቷዋል፤ የአፍሪካ ዋንጫም ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ ነው
እግር ኳስ 
እስከ መጨረሻው ውድድር እንዳጓጓ የዘለቀው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በማንችስተር ሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል። ማንችስተር ሲቲ ትናንት እሁድ በሜዳው ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 1 በሆነ ዉጤት አሸንፎ ዋንጫውን ከፍ ማድረግ ችሏል። እስከ መጨረሻው ሳምንት የእርሱን ነጥብ መጣል እየጠበቀ ሲከተለው የነበረው አርሴናል በሜዳው ያስተናገደውን ኤቨርተን 2 ለ 1 ቢያሸንፍም ከ20 ዓመታት በላይ ሲጠብቀው የነበረውን ዋንጫውን ማንሳት ሳይችል ቀርቷል። ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ለ4ኛ ተከታታይ ጊዜ በማንሳትም በሊጉ አዲስ ታሪክ መጻፍ ችሏል።

ርሴናል በሜዳው ያስተናገደውን ኤቨርተን 2 ለ 1 ቢያሸንፍም ከ20 ዓመታት በላይ ሲጠብቀው የነበረውን ዋንጫውን ማንሳት ሳይችል ቀርቷል።ምስል Odd Andersen/AFP/Getty Images

 

ክለቡ በሰባት ዓመታት ውስጥ 6ኛ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለ ቡድንም ሆኗል። በሊጉ በመጨረሻው ሳምንት ውድድሮች በአውሮጳ የውድድር መድረኮች የሚሳተፉ ክለቦችንም ለይቷል። 68 ነጥቦችን በመሰብሰብ በ4ኛነት ያጠናቀቀው አስቶን ቪላ የአውሮጳ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋግጧል።

68 ነጥቦችን በመሰብሰብ በ4ኛነት ያጠናቀቀው አስቶን ቪላ የአውሮጳ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋግጧል።ምስል Barrington Coombs/empics/picture alliance

ቶተንሃም ቀደም ሲል በሰበሰባቸው 66 ነጥቦች የአውሮፓ ልግ ዋንጫ ተሳትፎውን አረጋግጦ ነበር። በመቸረሻ ጫወታ በሜዳው ቦርንማውዝን ያስተናገደው ቼልሲ 2 ለ 1 በማሸነፍ የአውሮጳ ዋንጫ ውድድሮች መሳተፍ የሚያስችለውን ዕድል አመቻችቷል።

ከሜዳው ውጭ ብራይተንን የገጠመው ማንችስተር ዩናይትድ 2 ለ 0 ቢያሸንፍም ከአውሮጳ ዋንጫዎች ውድድር ውስጥ መግባት ሳይችል ቀርቷል። በሊጉ በርካታ ዋንጫዎችን በማንሳት ከፊት ካሉት የሚጠቀሰው ዩናይትድ በዓመት ያሳለፈው ደካማ ጊዜ በ8ኛ ደረጃ ለማጠናቀቅ ተገዷል። ይህም  በፕሪምየር ሊጉ ታሪክ ደካማው ውጤት ሆኖ ተመዝግቦበታል። በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሴፊልድ ዩናይትድ በርንሌይ እና ሉቶን ታወን በደታችኛው ሊግ የወረዱ ክለቦች ናቸው ።

ቡንደስ ሊጋ 
የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ዋንጫን ቀደም ብሎ ከፍ ያደረገው ባየር ሊቨርኩሰን የሊጉን ዓመት ባለመሸነፍ አጠናቋል። ሊቨርኩሰን በመጨረሻው የ34ኛው ሳምንት የሊጉ ጫወታ አውግስቡርግን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል። ነጥቡንም 90 በማድረስ አጠናቋል።

የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ዋንጫን ቀደም ብሎ ከፍ ያደረገው ባየር ሊቨርኩሰን የሊጉን ዓመት ባለመሸነፍ አጠናቋል።ምስል Michael Probst/AP Photo/picture alliance

ሊቨርኩሰን ሳይሸነፍ ሊጉን በመጨረስ ከአውሮጳ ኃያል ክለቦች ስማቸውን በወርቅ ከጻፉት የእንግሊዙ አርሰናል ፣ የጣልያኑኖቹ ኤሲ ሚላን እና ጁቬንቱስ ጋር ተቀላቅሏል። ክለቡ ከፊቱ ከፊቱ ከሚጠብቀውን የአውሮጳ ሊግ ዋንጫ የሚያሸንፍ ከሆነም የዣቮ አሎንሶ ቡድን ሌላ ታሪክ ይጽፋል። በቡንደስ ሊጋው ከአስር ዓመታት በላይ የሊጉን ዋንጫ በማሸነፍ ኃያል የነበረው ባየር ሙንሽን በመጨረሻው ሳምንት ጫወታ ከሜዳው ውጭ ሆፈንሃይምን ገጥሞ 4 ለ 2 ተሸንፏል። በዚህም ሊጉን በሶስተኛነት ለመጨረስ ተገዷል። 

በቡንደስ ሊጋው ከአስር ዓመታት በላይ የሊጉን ዋንጫ በማሸነፍ ኃያል የነበረው ባየር ሙንሽን በመጨረሻው ሳምንት ጫወታ ከሜዳው ውጭ ሆፈንሃይምን ገጥሞ 4 ለ 2 ተሸንፏልምስል Revierfoto/dpa/picture alliance

በሊጉ ቦሁም ፣ ኮሎኝ እና ዳርምሽታት ወደ ታችኛው ሊግ መውረዳቸውን አረጋግጠዋል። 
በመጨረሻም ፤ በኢትዮ - ጀርመን የባህል እና ስፖርት አስተባባሪነት ቅዳሜ እና እሁድ በኮሎኝ ከተማ ያስተናገደችው  በጀርመን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የእግር ኳስ ውድድር በኢትዮ በርሊን አሸናፊነት ተጠናቋል።

በሶስት ምድብ ተከፍሎ በአስራ ሁለት ቡድኖች መካከል ሲደረግ በነበረው ውድድር ኢትዮ ኮሎኝ ፣ አዲስ ፍራንክፈርት ፣ ኢትዮ ኑርንበርግ እና ኢትዮ በርሊን ለፍጻሜ ግማሽ የደረሱ ቡድኖች ናቸው ። ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈው ለፍጻሜ የደረሱት ኢትዮ በርሊን እና ኢትዮ አዲስ ፍራንክፈርት 2 መደበኛ የጫወታ ሰዓታቸውን አቻ በማጠናቀቃቸው በተሰጠ የመለያ ምት ኢትዮ በርሊን አዲስ ፍራንክፈርት ሁለትን 5 ለ 4 አሸንፎ ዋንጫ ወስዷል። 
 
ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW