ኢትዮጵያውያን ዳግም በብራስልስ አደባባይ ለተቃውሞ ሰልፍ
ሰኞ፣ ኅዳር 6 2014ማስታወቂያ
በተለያዩ የአውሮጳ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት ፋታ በኋላ ዳግም በአውሮጳ ሕብረት አደባባይ ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተዋል። ቤልጅየምን ጨምሮ ከጀርመን፣ ኔዘርላንድ፤ እና ፈረንሳይ የተሰባሰቡ እጅግ በርካታ መሆናቸው የተገለጸው እነዚህ ወገኖች የአውሮጳ ሕብረት በወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳይ አቋሙን እንዲፈትሽ ጥሪ አቅርበዋል። ዛሬ ብራስልስ ላይ ከአውሮጳ ሕብረት ጽሕፈት ቤት ፊትለፊት የተካሄደው ሰልፍ ከቅንጅት ጊዜ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካቶች የተሳተፉበት እንደሆነ በስፍራው የተገኘው የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ ገልጾልናል። ሰልፉ እየተካሄደ ባለበት ሰዓት ስልክ በመደወል አስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎችን አስተያየት ጠይቀናል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ