ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ
ዓርብ፣ ጥቅምት 1 2006ማስታወቂያ
የመጀመሪያው ዙር፣ ከነገ በስቲያ አዲስ አበባ ውስጥ የሚካሄድ ሲሆን፤ ሁለተኛውና የመጨረሻው ግጥሚያ አቡጃ ላይ ቅዳሜ ኅዳር 7 ቀን 2006 ይሆናል የሚካሄደው። ከሁለቱ ቡድኖች በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ የሚሆነው ስለሚያልፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በራሱ ሜዳ አስተማኝ ነጥብ ለማግኘት ጠንክሮ መጫዎት ይጠበቅበታል።
ከነገ በስቲያ እሁድ፣ አዲስ አበባ ላይ ለሚካሄደው ወሳኝ ግጥሚያ
የኢትዮጵያ ቡድን ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለጃፈር ዓሊ የገለጹት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው፣ አንድ ኣጥቂ ብቻ በጉዳት ምክኒያት መሰለፍ አለመቻሉን አረጋግጠዋል።
ለቡድኑ ፤ አንዱ ጥንካሬ ሰጪ ፣ የኳስ አፍቃሪዎች ድጋፍ መሆኑ አያጠራጥርም። ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የህዝብ አስተያየት አሰባስቦ ልኮልናል።
ጃፈር ዓሊ
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ