1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን የማበረታታት ጥረት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20 2016

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፤ ዘንድሮ ለሰብአዊ መብት መከበር ብርቱ ትግል ያደረጉትን ለመሸለም ሕዝብ ጥቆማ እንዲሰጥ ጠየቀ ። ማዕከሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመታገል አርዓያ የሆኑ ሦስት ሰዎችን በየዓመቱ ይሸልማል ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፤ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል ። ፎቶ፦ ከማኅደርምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፤ ዘንድሮ ለሰብአዊ መብት መከበር ብርቱ ትግል ያደረጉትን ለመሸለም ሕዝብ ጥቆማ እንዲሰጥ ጠየቀ ። ማዕከሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመታገል አርዓያ የሆኑ ሦስት ሰዎችን በየዓመቱ ይሸልማል ። ተቋሙ ከዚህ በፊት የሰብአዊ መብት ጥሰትን በመታገል መልካም ሥራ ሰርተዋል በሚል የተመረጡ ሰዎችን ለሁለት ዓመታት ሸልሟል ። ማዕከሉ  «እጅግ የከፋ ደረጃ ላይ ነው» ያለውን የወቅቱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ለሚጋፈጡ የሚሰጠው ሽልማት ዕውቅና መሆኑን ገልጿል ። ከዚያም ባሻገር  ሽልማቱ፦ለሰብአዊ መብት መከበር መታገል ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍል ብሎም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የመብት ጥሰት እየከፋ መምጣቱን ለማሳየት ጭምር የሚዘጋጅ  መሆኑን ተቋሙ አስታውቃል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በየአመቱ ተቋሙ የተመሰረተበትን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ለሰብዓዊ መብት መከበር በሰላማዊ ሁኔታ ለሚታገሉ ሦስት ሰዎችን እውቅና እና ሽልማት ይሰጣል።

ጥር መጨረሻ ላይ በሚያደርገው የተቋሙ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እውቅና እና ሽልማት ለሚያገኙት ሦስት ሰዎች ሕዝብ ከወዲሁ ጥቆማ እንዲሰጥ የተቋሙ ዋና ሥራ አሥኪያጅ አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልምስል Privat

"በኢትዮጵያ ውስጥ እስከዛሬ ሆኖ በማያውቅ ሁኔታ የሰብአዊ መብት አያያዝ እጅግ እጅግ የከፋ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ስለዚህ በዚህ አስከፊ የሚባል ችግር ባለበት ሀገር ውስጥ እንደገና ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ ሰዎች ደግሞ በዚያው ልክ ፊት ለፊት ተጋፋጭ ስለሆኑ ብዙ አይነት ጥቃት ይደርስባቸዋል"

በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ የሚደርሰው የመብት ጥሰት

ኢትዮጵያ ውስጥ የመብት ጥሰቶች አሳሳቢነት መጨመር በሀገር በቀል ሲቪክ ድርጅቶች ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በግለሰቦች፣ በዓለም አቀፍ የመብት ተቆርቋሪ ተቋማት እና ያገባናል ባይ ታዛቢዎች ተደጋግሞ ይገለፃል ፣ እርምት እንዲወሰድም ውትወታ ይደረጋል።

አሁን አሁን ግን ይባስ ብሎ ይህንን የሚያደርጉት እና ለሌሎች ምብት የሚቆረቆሩት ግለሰቦች የሌላ የመብት ጥሰት ተጋላጭ ሲሆኑ ይታያል። ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ የተባለ የሲቪክ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደለ ደርሰህ በዚህ ዐውድ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ፍርሃት ነግሷል ይላሉ።

"የሰብአዊ መብት ጥያቄ ውስጥ ነው ያለው። ሰዎች በሚናገሯቸው ለምን የሀሳብ ልዩነት አንፀባረቁ ተብለው እሥር ቤት ሲገቡ ታያለህ። ዛሬ የመናገር ነፃነት እየተገፈፈ ነው። ብዙ ሰዎች ከመናገር ዝምታን መርጠዋል። ፍርሃት ውስጥ ነው ያለው"

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ከ2010 ዓ. ም ጀሞሮ ያደረገውን የዳሰሳ ጥናት ከዚህ በፊት ይፋ አድርጓልምስል Solomon Muchie/DW

የመብት ጥሰት ፈጽመው በድርጊታቸው ተጠይቀው የታሰሩ ሰዎችን ቢኖሩ እንኳን የእነዚያን ሰዎች መብትም መጠበቅ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች መርህ ሆኖ ሲታይ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነበር የሚሉት አቶ ታደለ አሁን ላይ የታሰሩ የመብት መከበር አቀንቃኞችን የመጠየቅ ድፍረት እንኳን እየጠፋ መሆኑን በመግለጽ ለመብት ተሟጋቾች መሟገት ይገበል ይላሉ።

ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ላይ የሚፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን በተመለከተከ2010 ዓ. ም ጀሞሮ ያደረገውን የዳሰሳ ጥናት ከዚህ በፊት ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በግኝቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በሥራቸው ምክንያት ለግድያ፣ ለድብደባ ፣ ለዘፈቀደ እሥራት፣ ለግድያ ዛቻ እና ለማስፈራራት እንዲሁም ለስም ማጥፋት ዘመቻዎች ሰለባ እየሆኑ የመንቀሳቀስ ፣ ሀሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ መብቶቻቸው ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ እየተገደቡባቸው መሆኑን አመልክቶ ነበር።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሠ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW