1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ድርድር እንዲቀጥሉ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ ጥሪ አቀረቡ

እሑድ፣ ነሐሴ 10 2012

"ዘላለማዊው ወንዝ የሕይወት ምንጭ መሆኑን እንዲቀጥል በድርድሩ የሚሳተፉ ሁሉም ወገኖች በንግግር መንገድ እንዲቀጥሉ እጋብዛለሁ" ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አባይ "የሚያተባብር እንጂ የሚከፋፍል፤ ወዳጅነትን፣ ብልጽግናን እና ወንድማማችነትን የሚያለመልም እንጂ የጠላትነት፣ የአለመግባባት እና የግጭት" ሊሆን አይገባም ብለዋል።

Papst Franziskus Segen Ostersonntag Vatikan
ምስል፦ Reuters/A. Solaro

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ላይ የገቡበትን ውዝግብ በውይይት እንዲፈቱ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ -ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ ጥሪ አቀረቡ። በግድቡ የገቡበት ውዝግብ ወደ ግጭት ሊመራቸው እንደማይገባ ፍራንሲስ አሳስበዋል።

በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት የተጀመረው የሶስቱ አገሮች ንግግር በሱዳን ጥያቄ ለጊዜው ተቋርጧል። ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ሊካሔድ የታቀደው ድርድር በሱዳን ጥያቄ ለአንድ ሳምንት መራዘሙን ኢትዮጵያ አስታውቃለች።  የኢትዮጵያ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዳለው ድርድሩ በመጪው ሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሔዳል ተብሎ ይጠበቃል። 

"ዘላለማዊው ወንዝ የሕይወት ምንጭ መሆኑን እንዲቀጥል በድርድሩ የሚሳተፉ ሁሉም ወገኖች በንግግር መንገድ እንዲቀጥሉ እጋብዛለሁ" ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አባይ "የሚያተባብር እንጂ የሚከፋፍል፤ ወዳጅነትን፣ ብልጽግናን እና ወንድማማችነትን የሚያለመልም እንጂ የጠላትነት፣ የአለመግባባት እና የግጭት" ሊሆን አይገባም ብለዋል።ሊቃነ ጳጳሳቱ ይኸን ያሉት በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው የድንግል ማርያም የእርገት በዓል ሲከበር ባስተላለፉት መልዕክት ነው።   
 
ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ለረዥም አመታት በግድቡ ጉዳይ ድርድር ቢያደርጉም እስካሁን ከአግባቢ ሥምምነት አልደረሱም። የግብጹ ጠቅላይ ምኒስትር በዛሬው ዕለት ወደ ኻርቱም አቅንተዋል። ጠቅላይ ምኒስት አብደላ ሐምዶክ እንዳሉት ከጠቅላይ ምኒስትር ሙስጠፋ ማዶብሊ ጋር በሱዳን እና ግብጽ ግንኙነት እና የጋራ ጉዳዮች ላይ ይመካከራሉ። የግድቡ ጉዳይ እና ድርድሩ የደረሰበት ደረጃ ውይይት ይደረግበት እንደሁ የታወቀ ነገር የለም።

እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW