1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ መጀመሯ

ሰኞ፣ የካቲት 6 2015

መንግሥት እስከ አሁን ሱዳንና ኬንያን ጨምሮ ለስድስት ገዢ ሀገራት ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ የ3 ሚሊዮን ኩንታል ውል መፈረሙን አስታውቋል። የረድኤትና ሌሎች የሀገር ውስጥ ድርጅቶችም ከውጭ የሚገዙትን ስንዴ በሀገር ውስጥ እንዲተኩ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል የውል ስምምነት በመፈረም ላይ ነው ተብሏል።

Äthiopien | Oromia | Getreidelieferung
ምስል፦ Office of the PM of Ethiopia

ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ መዘጋጀቷ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ የውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም ላይ መድረሷን መንግሥት አስታወቀ።  የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ "እስከ አሁን ሱዳንና ኬንያን ጨምሮ ለስድስት ገዢ ሀገራት ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ  የ3 ሚሊዮን ኩንታል ውል መፈረሙን" መናገራቸው ተዘግቧል። የረድኤትና ሌሎች የሀገር ውስጥ ድርጅቶችም  ከውጭ የሚገዙትን በሀገር ውስጥ እንዲተኩ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል የውል ስምምነት በመፈረም ላይ ነው ተብሏል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ መንግሥት ትልቅ ውሳኔ ነው ብሎ እየሠራበት መሆኑን ደጋግሞ ከገለፀው ጉዳይ ስንዴን አምርቶ ለውጪ ገበያ መላክ የሚለው ይገኝበታል።ማንኛውም ሀገር ትርፍ ምርት ባይኖርም አለኝ የሚለውን ምርት ለውጭ ገበያ አቅርቦ ከዚህ ገበያ በሚያገኘው ገንዘብ የበለጠ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ ምርት ያስገባ ከሆነ በመርህ ደረጃ ምርትን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ከጉዳት በላይ ጥቅም ያለው መሆኑን የምጣኔ ኃብት ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ ገልፀዋል። ግን ይህ የሚሠራው የተሸጠው ምርት በሚያስገኘው ገንዘብ የሚገዛው እቃ የሚሸጠውን ምርት የላቀ ማሳደግ የሚችል ከሆነ ነው።
የሩሲያ እና የዩክሬንን ጦርነት እንደ ማሳያ የገለፁት ባለሙያው ሩሲያ ነጃጅ ለመሸጥ በጦርነቱ ጉዳይ የሀገሮችን አቋም እና ዝንባሌ ግምት ውስጥ ታስገባ ነበር። ይህም ማለት ምርቶች ከፖለቲካ አላማም ጭምር ለግብይት መቅረባቸው የገበያ ልማድ ነው ብለዋል። መንግሥት እስከ አሁን ሱዳንና ኬንያን ጨምሮ ለስድስት ገዢ ሀገራት ስንዴ ወደ ውጭ ለመላክ  የ3 ሚሊዮን ኩንታል ውል መፈረሙን አስታውቋል። አቶ ዋሲሁን በላይ ይህ ምርት ሳይተርፍህ ለገበያ የሚቀርብበት ገፊ ምክንያት እንደሆነ በምሳሌ ጭምር አስረድተዋል።ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ኢትዮጵያ በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ ዜጎቿ ከወራት በፊት ከዩክሬን ስንዴ በእርዳታ ቀርቦላታል። ዩክሬን ለኢትዮጵያ የለገሰችውን ስንዴ ጨምሮ ሌሎች ሀገሮች የለገሱት የእርዳታ እህል የተከማቸበትን አዳማ የሚገኘውን የአለም የምግብ ፕሮግራም ( WFP ) መጋዘንን የፈረንሳይ እና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጎብኝተውት ነበር። የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዋሲሁን በላይ ስንዴ ለውጭ ገበያ ሲቀርብ ለጉዳት የተጋለጠ ሕዝብ ከተዘነጋ አደጋ መሆኑን ጠቁመዋል። ሆኖም ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎቿ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ችግር እያለባቸውና አብዛኛው ሕዝብ ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጭ ሆኖም ቢሆን ኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት የምትሸጥ መሆኑ ምርት ሲተርፍ እና ከሀገር ውስጥ ፍጆታ በላይ ሲኖር ብቻ የሚደረግ ላለመሆኑ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

ምስል፦ Office of the PM of Ethiopia
ምስል፦ Office of the PM of Ethiopia

ሰሎሞን ሙጬ 

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW