1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድጋፍ ደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች 

ረቡዕ፣ ኅዳር 15 2014

ቀይ መስቀል በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ፣ የመድኃኒት ፣ የማረፊያ እና ሌሎች ድጋፎችን እየሰጠ መሆኑን ገልጿል። ቀይ መስቀል በትግራይ ክልል የሚያደርገው ድጋፍ በክልሉ ባሉ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ሳይቋረጥ መቀጠሉንም ተናግሯል። ሕወሓት በኃይል በያዛቸው የአማራ ክልል ከተሞች አሁንም ድጋፍ እያደረገ ነው ሆኖም የፀጥታ ሥጋት እክል ፈጥሯል።

Logo Ethiopian Red Cross Society
ምስል Ethiopian Red Cross Society

ድጋፍ ደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች 

This browser does not support the audio element.

በደብረ ብርሃን ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ጦርነት ያፈናቀላቸው ዜጎች ቁጥር ከ441 ሺህ መብለጡን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ገለፀ። ማሕበሩ በከተማው ለሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ፣ የመድኃኒት ፣ የማረፊያ እና ሌሎች ድጋፎችን እየሰጠ መሆኑን ገልጿል። ቀይ መስቀል በትግራይ ክልል የሚያደርገው ድጋፍ በክልሉ ባሉ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ሳይቋረጥ መቀጠሉንም ተናግሯል። ሕወሓት በኃይል በያዛቸው የአማራ ክልል ከተሞች አሁንም ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የገለፀው ማህበሩ ሆኖም በእነዚህ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሥጋት በሥራ ላይ እክል መፍጠሩንም ለዶይቼ ቬለ ነግሯል።የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ከሰሜኑ ኢትዮጵያ በተጨማሪ በወለጋ እና በመተከል በፀጥታ ችግር ፣ በቦረና በድርቅ ለጉዳት የተጋለጡትን እያገዘ እንደሚገኝና ይህንንም ለማጠናከር ሕዝብ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW