1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ በምርጫ ማግሥት

እሑድ፣ ሐምሌ 5 2007

የብይኑ-ፍጥነትና ይዘት፤ ከእስር የመልቀቁ ድንገተኝነት ኢትዮጵያዉያንን ጉድ አጃኢብ ከማሰኘቱ ጋር፤ «ብዙ እስረኞች እንዲፈቱ ኦባማ ኢትዮጵያን ብዙ ጊዜ ቢጎቦኙ ምናለ» አይነት ምፀት፤ እና «ጉብኝቱ ከምርጫዉ በፊት ቢሆን ኖሮ» ብጤ ሥላቅ እያናገረ ነዉ

ምስል DW/Y. Gebireegziabher

ኢትዮጵያ በምርጫ ማግሥት

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ የዘንድሮዉን ምርጫ በገዢዉ ፓርቲ የመቶ በመቶ ድል አጠናቅቃ፤ አዲስ አበባ ላይ ለምታስተናግደዉ ታላቅ ጉባኤ እየደገሰች፤ የታላቂቱን ሐገር ታላቅ መሪ (ፕሬዘደንት ባራክ ኦባማን) ለመቀበል ሽር-ጉድ እያለች ነዉ።በሁለቱ ታላላቅ መሰናዶዎች መሐል ሰሞኑን አዲስ አበባ ብዙ ያልተጠበቁ ሁለት ዕዉነቶች ተከስተዉባታል።የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ሰወስት ዓመት ያዘገመበትን የሙስሊም መሪዎችን ክስ በጥፋተኝነት መደምደሙ-አንዱ ነዉ።እንደ ሙስሊሞቹ መሪዎች ሁሉ በአሸባሪነት ክስ የተፈረደባት ርዕዮት አለሙ፤ በተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሱ ጋዜጠኞችና የአምደ መረብ ፀሐፍት (ጦማሪያን) መካከል አምስቱ፤ ቁጥራቸዉን በዉል ያላቅነዉ ነዉ የኦሮሞ ተማሪዎች ድንገት ከእስር መለቀቃቸዉ-ሁለተኛዉ ነዉ።

የብይኑ-ፍጥነትና ይዘት፤ ከእስር የመልቀቁ ድንገተኝነት ኢትዮጵያዉያንን ጉድ አጃኢብ ከማሰኘቱ ጋር፤ «ብዙ እስረኞች እንዲፈቱ ኦባማ ኢትዮጵያን ብዙ ጊዜ ቢጎቦኙ ምናለ» አይነት ምፀት፤ እና «ጉብኝቱ ከምርጫዉ በፊት ቢሆን ኖሮ» ብጤ ሥላቅ እያናገረ ነዉ።ለዛሬ ዉይይታችን የምፀቱን ሰበብ፤- መንደርደሪያ፤ የሥላቁን ምክንያትና ተያያዡን ጉዳይ ዋና ርዕስ አድረግነዋል።

ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW