1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ በስብዓዊ መብት ቀውስ ላይ ነች መባሉ

ሰኞ፣ ጥቅምት 19 2016

የፕሮፊሰር መስፍን ወልደ ማሪያም መታሰቢያ ፈውንዴሽን ባዘጋጀው ጉባዔ «ኢትዮጵያ በስብዓዊ መብት ቀውስ ላይ ነው ያለችው» ተባለ። በጉባኤዉ የፖለቲካ ችግርና ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በሰላምና በንግግር ለመፍታት አቅምና ሞራል ያጡ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ችግር አሁንም በየአካባቢው ጦርነት እየተካሄደ ሰው እየሞተና ህዝቦች እየተቸገሩ ነዉ።

የፕሮፊሰር መስፍን ወልደ ማሪያም መታሰቢያ ፈውንዴሽን
የፕሮፊሰር መስፍን ወልደ ማሪያም መታሰቢያ ፈውንዴሽን ምስል Hanna Demissie/DW

‘’ በኢትዪጵያ ከግዜ ወደ ጊዜ እየታየ የመጣው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሚያስደነግጥ ሁኔታ ተባብሶዋል’’

This browser does not support the audio element.

የፕሮፊሰር መስፍን ወልደ ማሪያም መታሰቢያ ፈውንዴሽን ባዘጋጀው ጉባዔ ላይ «ኢትዮጵያ የስብዓዊ  መብት ቀዉስ ላይ ነው ያለችው» ተባለ። በጉባኤዉ የፖለቲካ ችግርና ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ  በሰላምና በንግግር  ለመፍታት አቅምና ሞራል ያጡ ፖለቲከኞች በሚፈጥሩት ችግር አሁንም በየአካባቢው ጦርነት እየተካሄደ ሰው እየሞተና ህዝቦች በስላም እጦት እየተቸገሩ መሆኑ በዝርዝር ተነስትዋል ።የስብዓዊ መብት ይዞታ በኢትዮጵያ

የሰባዊ መብቶች ሁኔታ እና ተጠያቂነት በሚል በተዘጋጀው የ ዘንድሮ ጉባኢ፣ ባለፍት ዓመታት  የማህበሪዊ እና የስብአዊ መብት ጥሰትን ለመመርመር   በርካታ እንቅፍቶች  ነበሩ ሲሉ ችግሮችን በመረጃ እና በማስረጃ ያቀረቡት ከኢትዮጰያ የስብዓዊ መብት ኮምሽን የኤኮኖሜ እና የስብአዊ መብት ዳይሪክተር  ዶ/ ብራይት ማን  ገ/ኪዳን፤ ስዎች በሀገራቸው የመስራት፣ ንብረት የማፍራት ፣ህክምና የማግኝት፣  የመማር እና መረጃን የማግኝት መብታቸው ሲጣስ እየታየ  መረጃን ለመስብስብ  አስቸጋሪ እንደነበር አስረድተዋል። በሃገሪቱ አንዳንዶቹ የመብት ጥሰቶችን  የሚፈፅሙት  ህግን ከለላ አድርገው እንደሆነ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ያሉ አብዛኛው  ማህበራት ትኩረት በፖለቲካዊ መብት ላይ ያተኮሩ ከመሆናቸው ባሻገር  የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሰባዊ መብት  እውቀት እና ግንዛቤ ክፍተት መኖሩ  እንቅፋት ሆነውብናል ሲሉ ተናግረዋል።በወላይታ ተፈጸሟል የተባለው የስብዓዊ መብት ጥሰትና የኢሰመጉ መግለጫ

አሁን በኢትዮጵያ ይለው ችግር የመብት መከበር  ቀርቶ በስላም ውጥቶ ለመግባት እንኩዋን ዋስትና ይሚስጥ መንግስት ነው የቸገረው ሲሉ  የተናገሩት የህግ ባለሙያው አቶ ሙሉጌታ አረጋዊ  ናቸው ‘’የህግ ባለሙያው የመብት ጥሰቶችን  ይፈፅማል የተባለው መንግስት  ከማህበረሰቡ የወጣ ነው  ያልዘራነውን አናጭድም  ሲሉ  እንደማህበረሰብ ለችግሮቹ መፍትሄ ወደራሳችን  መምልከት ‘’ አለብን ብለዋል ።  በፕሮፌሰር መስፍን የተመስረተው የኢትዮጵያ ስብዓዊ መብት ጉባዔ  ባለፍት 32 ዓመታት በማህበራዊ ና ፖለቲካዊ መብት ላይ በርካታ ስራዎችን ሰርትዋል። የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ  ምክትል ዳይሪክተር አቶ ተስፋዬ ገመቹ ‘’ በኢትዪጵያ ከግዜ ወደ ጊዜ እየታየ የመጣው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሚያስደነግጥ ሁኔታ ተባብሶዋል’’ ብለዋል።

የፕሮፊሰር መስፍን ወልደማሪያም ፍውንድሽ  በቅርቡ ያለፍርሀት በልበ ሙሉነት ሳይስለቹ እና ሳይታክቱ ህይወታችውን  ለሀገራቸው የስጡትን የፕሮፌስር መስፍን ወልደማሪያምን መኖሪያ ቤት እና  ስራዎቻቸውን ለህዝብ ክፍት እንሚደሚሆን ተናግረዋል። የፕሮፊሰር መኖሪያ የነበረውን ቤት  ያስረከባቸውን የቤቶች  ኮርፕሪሽንም አመስግነዋል።

ሃና ደምሴ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW