ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ የወሰደችው አቋም ተወደሰ
ሐሙስ፣ የካቲት 19 2012
ማስታወቂያ
ስለ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ እና በሱዳን መካከል ዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ ሊካሄድ የነበረው ድርድር ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ኢትዮጵያ መጠየቋ ትክክል መኾኑን ኹለት ምሑራን ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናገሩ። ኢትዮጵያ ጥቅሟን የማያስከብር ውል በፍጹም መፈረም እንደሌለባት በርካታ ኢትዮጵያውያን ሲያሳስቡ ቆይተዋል። የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የአባይን ባለቤትነታችንን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ውል ኢትዮጵያ ፈጽሞ መፈረም የለባትም ብለዋል ምሑራኑም። አክለውም፦ በዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ አደራዳሪነት የሚካሄደው ውይይት የቀጠናው ሃገራትን ቃኚ የፖለቲካ አቅጣጫን እየያዘ ስለመጣ ኢትዮጵያ ስልታዊ ማፈግፈግ እያደረገች ይመስላል ብለዋል።
መክብብ ሸዋ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
መክብብ ሸዋ