ኢትዮጵያ በእግርኳስ ግጥምያ ኮትዲቯርን 2 ለ1 ረታች
ማክሰኞ፣ ኅዳር 9 2012ማስታወቂያ
ዛሬ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደዉ የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን የኮትዲቯር ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድንን 2 ለ 1 አሸነፈ። ሦስቱም ግቦች በመጀመርያዉ አጋማሽ ከግብ ያረፉ ሲሆን፤ የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዉ በተጀመረ በሦስተኛዉ ደቂቃ የመጀመርያዉን ግብ በማስቆጠር ለጥቂት ደቂቃዎች መሪ መኾን ችሎ ነበር። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ቡድን ሁለት ጎሎችን በሱራፌል ዳኛቸውና በሺመልስ በቀለ ከመረብ በማሳረፍ መሪነቱን መንጠቅ እና አሸናፊ መኾን ችሏል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከዚህ በፊት በማደጋስካር አቻው አንድ ለባዶ መሸነፉ ይታወሳል።
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ