ኢትዮጵያ በዓለም 2025 መዘርዝር ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገር ተባለች
ዓርብ፣ ነሐሴ 23 2017
ኢትዮጵያ በዓለም መዘርዝር - በ 2025 ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ሰላም ያለባት ሀገር መባልዋ
ዓለም አቀፉ የምጣኔ ሀብት እና የሰላም ጥናት ተቋም (IEP) ባወጣው ዓመታዊ "ዓለም አቀፍ የሰላም መረጃ ጠቋሚ" ዘገባ ኢትዮጵያ ደካማ የሰላም ሁኔታ ያላት ሀገር መሆንዋን ገለፀ። ጥናቱ በዘንድርዉ የ2025 ዘገባው የሀገራትን የሰላም ሁኔታ ለማመልከት 23 የሚሆኑ የጥራት እና የመጠን አመልካቾችን ተጠቅሟል።በዚህ መሰረት በዚህ ዓመት ከተመለከታቸው 163 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ 138ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ኤርትራ በ132ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።ኢትዮጵያና ኤርትራ በአዋሳኝ ድንበር አካባቢዎች፥ የነዳጅ እጥረት
በአፍሪካ አህጉር 44 ሀገራት በጥናቱ የተካተቱ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ 36ኛ ኤርትራ ደግሞ 32ኛ ሆናለች።ዶሞክራቲክ ኮንጎ 44ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።በሪፖርቱ መሰረት ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪቃ ሀገራት የሚገኙበት ቀጣና የሰላም እጦት ያለበት ቀጠና ሲሆን፤ በዚህ ቀጠና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ዝቅተኛ የሰላም ያላት ሀገር ተብላለች። የዓለም አቀፍ የሰላም መረጃ ጠቋሚ የጥራት እና የመጠን የሰላም መረጃ ጠቋሚ ነጥቦችን እና አመላካቾችን በመጠቀም የሀገራትን የሰላም ሁኔታ ከ1-5 ነጥብ ሰጥቷል።ጥቃት፣ግጭት እና ግጭት ያስከተለው የኢኮኖሚ ድቀት ከመስፈርቶቹ መካከል ናቸው።የግጭት ተጋላጭነት ምክንያቶችና የሰላም ሚኒስቴር ማብራሪያ
ኢትዮጵያ በአብዛኛዎቹ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አስተዳደር የትጥቅ ግጭቶችን እያስተናገደች ሲሆን፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እስኪቋጭ ድረስ ከጎርጎሪያኑ ከ2020 እስከ 2022 በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል፣ከጎርጎሪያኑ ነሀሴ 2023 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ የፌደራል መንግስቱ ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር የትጥቅ ግጭት ውስጥ ገብቷል።በኦሮሚያ ክልልም ከስድስት ዓመታት በላይ መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሃይሎች ከክልሉ እና ከፌደራል መንግስት ጋር ሲፋለሙ ቆይተዋል። ምዕራብ እና ማዕከላዊ አውሮፓ ሰላም የሰፈነበት ክልል የተባለ ሲሆን፤ አይስላንድ በቀጠናው በጣም ሰላም የሰፈነባት ሀገር ተብላለች።
ገበያዉ ንጉሴ / አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ