1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሠላም ተስፋ ጥንቃቄ

ሐሙስ፣ ሰኔ 14 2010

ቃል በጎዉ ተስፋ ለዉጤት እንዲበቃ ግን አቶ አብዱረሕማን ሰዒድ እንደሚያምኑት ዋስትና ያስፈልጋል።ዋስትናዉ በአቶ አብዱረሕማን እምነት ኢትዮጵያ የታየዉ ለዉጥ ኤርትራንም «ሲደባብስ» ነዉ።አለበለዚያ ቃል ተስፋዉ ዘላቂ ሠላም አያመጣም።የወይዘሮ ርብቃ አስተያየትም ተመሳሳይ ነዉ

Eritrea Präsident Isaias Afwerki
ምስል Eritrea Minister of Information/Y.G. Meskel

NMII - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት የሁለቱን ሐገራት የድንበር ዉዝግብ ለማስወገድ ሰሞኑን ያሳዩት መቀራረብ ከሁለቱ ሐገራት አልፎ ለአካባቢዉም ሠላም እንደሚጠቅም የተለያዩ ወገኖች እያስታወቁ ነዉ።ዉጪ የሚኖሩ የኤርትራ የሠብአዊ መብት ተሟጋቾች እና የፖለቲካ አቀንቃኞችም ሁለቱ መንግሥታት ያሳዩትን መቀራረብ 20 ዓመት የደፈነዉን ግጭት እና ዉዝግብ ለማስወገድ «ተስፋ ሰጪ» ይሉታል።ይሁንና የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ያደረጉትን ንግግር እና ቃል ገቢራዊትን በጥንቃቄ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ መክረዋል።

አዲስ አበባ ባለፉት 27 ዓመታት የማሆኑ የሚመስሉ ሁነተኖችን ማሰማት፤ማስተናገድ ከጀመረች ሰወስት ልትደፍን አስር ቀን ቀራት።ዛሬም ቀጥላለች።ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ  አሕመድ የሚመሩት ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ ባለፈዉ ግንቦት 28 ያሳለፈዉ ዉሳኔ ደግሞ ምናልባት የመቶ ሺዎች ሕወት፤ደም፤ እና አጥንት የተገበረበትን ጦርነት «ለነበር ዝክር» ከቤተ-መዘክር የሚከት ነዉ።

ምስል DW/Y.Geberegziabher

ይላሉ ኤርትራዊቱ ሰብአዊ መብት ተሟጋች ወይዘሮ ርብቃ ስብሐቱ።ኤርትራዊዉ የፖለቲካ አቀንቃኝ እና ኃያሲ አብዱረሕማን ሰዒድም መቀራረቡ የ16 ዓመታቱን ሠላምም-ጦርነትም የለም ግንኙነትን ከፍፃሜዉ የሚያደርስ ሊሆን ይችላል ባይ ናቸዉ።የመቀራረቡ መሠረት እና ምክንያት ወይዘሮ ርብቃ እንደሚያምኑት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ናቸዉ።«የእግዚአብሔር ስጦታ» ይሏቸዋል።

                      

ቃል በጎዉ ተስፋ ለዉጤት እንዲበቃ ግን አቶ አብዱረሕማን ሰዒድ እንደሚያምኑት ዋስትና ያስፈልጋል።ዋስትናዉ በአቶ አብዱረሕማን እምነት ኢትዮጵያ የታየዉ ለዉጥ ኤርትራንም «ሲደባብስ» ነዉ።አለበለዚያ ቃል ተስፋዉ ዘላቂ ሠላም አያመጣም።የወይዘሮ ርብቃ አስተያየትም ተመሳሳይ ነዉ።ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እንዲቀራረቡ የሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ነገስታት አስተዋፅኦ ማድረጋቸዉ በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የፖለቲካ አቀንቃኝ አብዱረሕማን ሰዒድም ይሕን ሐሳብ ይጋራሉ።ይሁንና ቱጃሮቹ ነገስታት ኢትዮጵያ እና ኤርትራን ከማግባባት ባለፍ በመካከለኛዉ ምሥራቅ ዉጥንቅጥቅ  እንዳይከቷቸዉ፤ አቶ አብዱረሕማን እንደሚመክሩት፤ የአዲስ አበባ እና የአስመራ ፖለቲከኞች መጠንቀቅ አለባቸዉ።

                                    

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአዋሳኝ  ግዛት ይገባኛል ሰበብ ከ1990 እስከ 92 በገጠሙት ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከ80ሺሕ በላይ ወጣት አልቋል ተብሎ ይገመታል።በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ቆስሏል።በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር የድኾቹ ሐገራት ጥሪት ወድሟል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የሁለቱ ሐገራት ጦር ዛሬም ደቡብ እና ሰሜን እንደተፋጠጠ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW