ኢትዮጵያ እና የሁለቱ ሱዳኖች ሽምግልና
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 25 2005ማስታወቂያ
ነገ አዲስ አበባ ውስጥ የሚካሄደው የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ውይይት የተሳካ ውጤት ያስገኛል ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ኢትዮጵያ አስታወቀች ። ሁለቱ መሪዎች አዲስ አበባ ውስጥ እንዲነጋገሩ የጋበዘችው ኢትዮጵያ የተጋታው የሱዳን የሠላም ጥረት ወደፊት ይራመዳል የሚል አዎንታዊ አስተያየት እንዳላት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ሁለቱ መሪዎች አዲስ አበባ እንዲነጋገሩ የጋበዙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ና የአፍሪቃ ህብረት መሪዎቹ በመስከረም የደረሱበት ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ። በሠላሙ ጥረት የኢትዮጵያን ሚናና ከውይይቱ ስለሚጠበቀው አምባሳደር ዲና ሙፍቲን በስልክ አነጋግረናችዋል ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ