1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«ኢትዮጵያ ዉስጥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ ለሚሰሩ በቂ ትኩረት አልተሰጠም»

ሐሙስ፣ ሰኔ 26 2017

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ያሉ ሰራተኞች ከመንግስት እና ከክልል ባለስልጣናት በቂ ትኩረት እያገኙ እንዳልሆነ አቶ ግፋወሰን ተናግረዋል። በእነዚህ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ያሉ ሠራተኞች በወር ከ26 እስከ 30 ዶላር ያገኛሉ። ሰባት ወይም ስምንት ሠራተኞች በትናንሽ ክፍሎች ተከራይተዉ በጋራ ይኖራሉ። አብዛኛዎቹ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይደርስባቸዋል።

«ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሰራተኞች በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ ለሚሰሩ በቂ ትኩረት አልተሰጠም»  አቶ ግፋወሰን  ማርቆስ
አቶ ግፋወሰን  ማርቆስምስል፦ Privat

«ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሰራተኞች በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ ለሚሰሩ በቂ ትኩረት አልተሰጠም»

«ኢትዮጵያ ዉስጥ ለመንግሥት ሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞወዝ ወለል አለ። ግን ለግል ባለሃብቶች የንግድ ተቋም ዝቅተኛ የደሞወዝ ወለል የለም። በሕግ ደረጃ ይፋ እንደተነገረዉ፤ 2019 ዓ.ም. በወጣዉ አዲሱ የሥራ አዋጅ መሰረት ዝቅተኛ የደምወዝ ወለል ቦርድ ተዋቅሮ ይወሰናል የሚል ነገር ነበር። ሆኖም ግን ላለፉት ስድስት ዓመታት እስካሁን፤ ቦርድ አልተቋቋመም ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልም አልተሰራም። ስለዚህ ያ በሌለበት ሁኔታ ባለሃብቱ በፈለገበት የወለል መጠን ሰራተኛን መቅጠር ይችላል ማለት ነዉ። » አቶ ግፋወሰን ማርቆስ

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ ያሉ ሠራተኞች ከመንግስት እና ከክልል ባለስልጣናት በቂ ትኩረት እያገኙ እንዳልሆነ አቶ ግፋወሰን ተናግረዋል። በእነዚህ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ያሉ ሠራተኞች በወር ከ26 እስከ 30 ዶላር ያገኛሉ። ሰባት ወይም ስምንት ሠራተኞች በትናንሽ ክፍሎች ተከራይተዉ ገባራ ይኖራሉ። አብዛኛዎቹ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይደርስባቸዋል።  ሠራተኞቹ ከሚያገኙት ዝቅተኛ ደመወዝ በተጨማሪ፣ በሀገሪቱ ባለው የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ምክንያት ተቸግረዋል።

ግፋወሰን ማርቆስ  በጀርመን የዶቼ ቬሌ የራድዮ ጣብያ ዋና መሥርያ ቤት በሚገኝበት በቦን ከተማ ዩንቨርስቲ ዉስጥ በልማት ምርምር ጥናት ማዕከል Center for developenet research ዉስጥ ለዶክትሪት ዲግሪ በምርምር ሥራ ላይ ይገኛሉ። ግፋወሰን ማርቆስ በተቋሙ ዉስጥ የሚያካሂደዉ ጥናት በፖለቲካ ኤኮኖሚ፤ ልማት ብሎም በኅብረተሰብ ጥናት ላይ የተኮረ ነዉ።  በተለይም በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዉስጥ የሚገኙ ሠራተኞችን የኑሮ ሁኔታ ከዛም ባለፈ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ባሉት የሰራተኛ ማህበራት ላይ ጥናቱ እንደሚያተኩር አቶ ግፋወሰን ማርቆስ ተናግረዋል።

ሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ምስል፦ Gifawosen Markos

በወላይታ ተወልደው ወላይታ ዉስጥ ባለች ቦዲቲ በተባለች ከተማ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ግፋወሰን ማርቆስ ፤ የመጀመርያ ዲግሪያቸው በጅማ ዩንቨርስቲ ፤ በልማት ጥናት ዘርፍ ፤ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን መጀመርያ በጀርመን ሃገር በዓለም አቀፍ ፖለቲካል ኢኮኖሚ /Global Political Economy/በመቀጠል በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ጀምረውት የነበረዉን በክልል እና የአካባቢ ልማት ጥናት Regional and local development studies የማስትሪት ዲግሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው ሁለተኛ የማስትሪት ዲግሪ ባለቤት ናቸው። በወልቂቴ ዩንቨርስቲ መምህርም ነበሩ።

አቶ ግፋወሰን ማርቆስ ለሰጡን ቃለምልልስ በዶቼ ቬለ ስም በማመስገን ፤ ሙሉዉን ጥንቅር እንዲያደምጡ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW