ኢትዮጵያ ዉስጥ የቴክኒክና የሙያ ተማሪዎች ቁጥር እያሽቆለቆለ መሆኑ ተነገረ
ረቡዕ፣ ግንቦት 27 2017
ኢትዮጵያ ዉስጥ የቴክኒክና የሙያ ትምህርት የሚያጠኑ ተማሪዎች ቁጥር እያሽቆለቆለ መሆኑ ተነገረ።የጥራት ችግርና ዘርፉን የሚቀላቀሉ ሰልጣኞች ዝቅተኛ ዉጤት ያላቸዉ ተማሪዎች መሆን ለዘርፉ ወጤታማ አለመሆን ምክኒያት ነዉ ይባላል።ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገቡተዉ የመማር ፍላጎት ያላቸዉ ተማሪዎች ቁጥር በእጅጉ እየቀነሰ ነዉ ተብሏል።የስራና ክሂሎት ሚንስቴር በበኩሉ አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ተማሪዎች በኮሌጆች ገቡተዉ እየሰለጠኑ ነዉ ይላል።
ሰልጣኝ ተማራዎችን እያጡ የመጡ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በኢትዮጵያ
በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አዞን አስተዳደር የሚገኘውን የኬሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2-017 የትምህርት ዘመን ከ400 በላይ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር ስራ ቢጀምርም 50 ተማሪዎችን ብቻ ማግኘት እንደቻለ ነው የኮሌጁ ዲን አቶ ሙክታር ገዝሃኝ የሚናገሩት <እኛ በትምህርት ዓመቱ ወደ 400 ተማሪዎችን ለመቀበል ነበር የሰራነው ግን ያገኘ ነው 50 ተማሪ ነው በዚህ ዓመት>
በተመሳሳይም በኦሮሚያ ክልልም አምቦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መምህር የሆኑት መምህር ለሚ እንደሚገልጹት ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚወጣው ፖሊሲ በየጊዜው የሚቀያየርና ገና ያልተጠናቀቀ መሆን ለተማሪዎቹ ፍላጎት ማጣት ምክንያት ነው ይላሉ፡፡<ፖሊሲያችን ከባድ ክፍተት አለበት ለምሳሌ፡- ዘንድሮ ምትቀበላቸው ተማሪዎች አሉ እነዚያ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተምረው ሳይጨርሱ ሌላ ፖሊሲ እንደገና እንተገብርባቸዋለን ገና ተሞክሮ አላለቀም ፖሊሲያችን>
በወ/ሮ ሲህን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅመምህር የሆኑት አቶ ሰለሞን ፈንታው በበኩላቸው 12ኛ ክልልን ካጠናቀቁ በኋላ ተማሪዎች ወደ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ገብተው የመማር ፍላታቸው ዝቅተኛ ነው ይላሉ።<12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ 20/80 ይመጣሉ ብለን ነው እ ምንጠብቀው 80/100ዎቹ ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ይገባሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው ከዚያ ውስጥ 80/100 መንግስታዊ በሆኑ ኮሌጆች ይገባሉ ተብሎ ቢጠበቅም 20/100 እንኳን የሚገባ የለም፡፡>
የመምህራን ያለስራ መቀመጥ
በፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎች በቁጥር ዝቅተኛ መሆንና |የዘርፉ በተማሪዎች ተመራጭ አለመሆን ለበርካታ መምህራን ስራ መፍታት ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ <አንዳንድ ኮሌጆች ተዘግተዋል አሁን አካባቢን መሰረት ያደረጉ ስልጠና ስለሆነ የምንሰጠው ከዚያ ውጭ ባለው እኛም ተማሪ ቢመጣ አንቀበልም መምህራኖቹ ግን ያው እንደትርፍ ተቀምጠዋል እኛም ለክልል አሳውቀናል፡፡>
አሁን በፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎች ስልጠና ከጀመሩ በኋላ ያቋጣሉ የሚለው ተማሪ ሀይለሚካኤል እረታ ጥራት ያላቸው መምህራን ማግኘትና የተግባ ር ስልጠናዎቹ ያልተሟሉ አለመሆን ለተማሪዎቹ ማቋረጥ ምክንያት ነው ይላል፡፡ <እኛ ክፍል ስንጀምር 30 ተማሪዎች ነበርን ከዚያ 12 ቀረን የምትፈልገው ነገር ተሟልቶ የሚሰጥ ተቋም አታገኝም ከመምህራን ጀምሮ ጥራት ያለው ሊጎድል ይችላል፡፡>
በአማራ ክልል 12ተኛ ክፍልን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ማነስ
በአማራ ክልል ከተማሪዎች ፍላት ማጣት ይልቅ በወቅቱ በክልልሉ ያለው የሰላም እጦት የተማሪዎች መደበኛ ትምህርትን ተከታትሎ አለማጠናቀቅ አንዳንድ ኮሌጆች ተማሪዎች ለማጣታቸው ምክንያት መሆኑን አቶ ሙላው ልመነህ የአማራ ክልል ስራና ስልጠና ቢሮ የተቋት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ይናገራሉ፡፡<12ኛ ክፍል የሚጨርሰው ሰልጣኝ ቁጥር እንደሚታየው እንደሀገር ዝቅተኛ ቁጥር ነው በዚህ በአማራ ክልል ባሉ ገጠር ወረዳዎች አሁን ላይ 12ኛን ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን ስናይ የመቀነስ አዝማሚያ አለው>
የስራ እና ክህሎት ሚኒስተር በበኩሉ አሁን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚታየው የመደበኛ ስልጠና ተማሪዎች መቀነስ የዘርፍ መቀየር ነው እንጅ ተማሪዎቹ በአጫጭር ስልጠናዎች እየበቁ ነው ይላሉ አቶ ሙህዲን አባሞጋ በሚኒስቴሩም የቴክኒክና ሙያ ዘርፈ የተቋማት አቅም ግንባታ መሪ ስራ አስፈጻሚ<የፍላጎት ወይም የዘርፍ መቀየር ነው እንጅ በአጠቃላይ የሰልጣኝ ቁጥር መቀነስ አይደለም የመደበኛ ሰልጣኝ ይን ያህል ቢሆንም የአጫጭር ስልጠና ሰልጣኖች የዚህን 3እና 4 እጥፍ ይኖራል፡፡>
በተለይም ተማሪዎች በመደበኛ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገብተው መማር ያለመፈለግ ለበርካታ መምህራን ከስራ ውጭ መሆን ምክንያት ሁነዋል ስንል የጠየቅናቸውን አቶ ሙህዲን አባጋሞ በወቅቱ ይህንን አይፈቅድም ብለዋል፡፡ <እኛ አሁን ባለን በየተቋቱ የሚሰራው የረፎርም እንቅስቃሴ ሰዎችን ስራ አስፈትቶ ያስቀምጣል የሚል ግምት የለንም በጣም የተለያዩ ኢንሸቲቮች በየተቋቱ እየተሰሩ ነው» ያሉት፡፡
ኢሳያስ ገላዉ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ