1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ውስጥ ከተጠለሉ ስደተኞች 40 ያክል ሞቱ

ሐሙስ፣ መስከረም 10 2016

ኮሚሽኑ በቅርብ ጊዜ አደርግሁት ባለው ክትትል "በስደተኞች ሠፈሮች ውስጥ የከፋ ሰብዓዊ ሁኔታ እና የምግብ አቅርቦት እጥረት እየጨመረ መምጣቱን አሳሳቢ ብሎታል።የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የርዳታ ድርጅቶች ለስደተኞች ይሰጡት የነበረዉን ሰብአዊ ርዳታ ማቋረጣቸዉን አስታዉቋል።

የደቡብ ሱዳን ስደተኞች-ጋምቤላ ሠፈራ ጣቢያ
ጋምቤላ የሰፈሩት የደቡብ ሱዳን ስደተኞችምስል DW/Coletta Wanjoyi

«ኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞች ይዞታ አሳሳቢ ነዉ»ኢሰመኮ

This browser does not support the audio element.

ምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ጎንደር ዉስጥ ከሰፈሩ የዉጪ ስደተኞች 40 ያክሉ በረሐብና በበሽታ መሞታቸዉ ተነገረ።የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሐገሪቱን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ መስሪያ ቤትን ጥቅሶ እንደዘገበዉ ጋምቤላ ዉስጥ 30 ስደተኞች በረሐብና ከረሐብ ጋር በተያያዘ በሽታ ሞተዋል።ጎንደር ዉስጥ ደግሞ በኮሌራ በሽታ 9ኝ ስደተኞች ሞተዋል።ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በየአካባቢዉ ለሰፈሩ ስድተኞች የሚሰጡት ርዳታ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎች አስታዉቋል።የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የስደተኞቹን ይዞታ «አሳሳቢ» ብሎታል።የሱዳን ተፈናቃዮች በምዕራብ ጎንደር


ኮሚሽኑ በቅርብ ጊዜ አደርግሁት ባለው ክትትል "በስደተኞች ሠፈሮች ውስጥ የከፋ ሰብዓዊ ሁኔታ እና የምግብ አቅርቦት እጥረት እየጨመረ መምጣቱን አሳሳቢ ብሎታል።የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የርዳታ ድርጅቶች ለስደተኞች ይሰጡት የነበረዉን ሰብአዊ ርዳታ ማቋረጣቸዉን አስታዉቋል።

ከዓለም አቀፍ የተራድዖ ድርጅቶች ለስደተኞች ይቀርብ የነበረው ሰብዓዊ ድጋፍ ከጊዜ ጊዜ እየቀንሰ መጥቶ በአሁኑ ሰዓት የምግብ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ መቆሙን ለዶቼ ቬለ ያረጋገጠው የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎ ችግሩ የተከሰተው ኃላፊነት ያለባቸው የተራድዖ ድርጅቶች ድጋፍ መስጠት በማቋረጣቸው መሆኑን ገልጿል።ኢትዮጵያ የሚገቡ የሱዳን ስደተኞች
በጋምቤላ ክልል ውስጥ ከ30 ያላነሱ ስደተኞች በረሃብና በምግብ እጦት መሞታቸውን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት እንደገለፀለት ኢሰመኮ የገለፀ ሲሆን ከሀገራቸው ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ ሱዳናዊያን ስደተኞች መካከል ዘጠኝ ያህሉ ምዕራብ ጎንደር ዞን ውስጥ በተቋቋመው የኩመር መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በኮሌራ ወረርሽኝ መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ( UNHCR ) ከሰሞኑ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከተጠለሉ የኤርትራ ስደተኞች በከፊልምስል TIKSA NEGERI/REUTERS


"የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ሰብዓዊ ሁኔታ እያሽቆለቆለ ነው" - ኢሰመኮ 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት እና ከጎረቤት ሀገራት ወደ አማራ፣ ቤንሻንጉል-ጉሙዝ፣ ጋምቤላ እና ሶማሌ ክልሎች የሚደረገው ስደት በመጠለያ ጣቢያዎች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መባባስ ምክንያት መሆናቸውን መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ. ም ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
በጋምቤላ ክልል ያለው የጸጥታ ችግር የስደተኞችን ፈተና የበለጠ አባብሶታል ያለው ኢሰመኮ ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያዎች ውጪ ምግብ ፍለጋ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የስደተኞች ጥቃት አባብሶታል ሲል በምርመራ ግኝቱ አምልክቷል።ኤርትራዉያን ተገን ጠያቂዎችና የሱዳን ስደተኞች በሊቢያ
ይህን መሰሉ ችግር ወትሮውንም በእርስ በርስ ግጭት፣ በድርቅ እና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት እስከ 20 ሚሊዮን ዜጎቿ እርዳታ ጠባቂ ለሆኑባት ኢትዮጵያ ሌላ ችግር ማስከተሉ እንደማይቀርም ይታመናል።
ኢሰመኮ የኢትዮጵያ መንግስት እና የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ የተራድዖ ድርጅቶች ለስድተኞች የሚቀርቡትን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያስቀጥሉ ኮሚሽኑ መጠየቁን ለዶቼ ቬለ ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጡት የተቋሙ የስደተኞች፣ ሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እናፍልሰተኞች መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር እንጉዳይ መስቀሌ ተናግረዋል።


ለስደተኞች ከለላ የመስጠት ግዴታ 

ከተለያዩ ሀገራት የመጡ 1 ሚሊየን የሚሆኑ ስደተኞችን አስጠልላለች ፣ ከለላ እንዲሁም ጥበቃም ታደርጋለች የምትባለው ኢትዮጵያ ከአለም አቀፍ ረጂዎች የሚቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ የማስተባበር እንጂ ለስደተኞች ምግብ የማቅረብ ኃላፊነት ወይም ግዴታ እንደሌለባት የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ለዶቼ ቬለ ገልጿል። የተቋሙ የኮሙኒኬሽን እና ውጫዊ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ በአካል ንጉሴ ችግሩ የተከሰተው ድጋፉን እንዲያቀርቡ ኃላፊነት ያለባቸው ዓለም አቀፍ የተራድዖ ድርጅቶች ድጋፍ መስጠት በማቋረጣቸው መሆኑን ገልፀዋል።
።።።።።። 

ኢትዮጵያ ውስጥ ከተጠለሉ ስደተኞች መካከል 30 በጋምቤላ 9 በጎንደር ሞተዋል ተባለ። ወቅታዊው የሱዳን ቀውስ የሀገሩን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያዊ በሁለት አቅጣጫ ለመፈናቀል ዳርጓል።
በአማራ ክልል በመተማ በኩል ኩመር በተባለ ስፍራ እንዲሁም በቤኒሻንጉል - ጉሙዝ ክልል ኩርሙክ በሚባል አካባቢ 36 ሺህ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ገብተዋል ያሉት የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት የኮሙኒኬሽን እና ውጫዊ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ በአካል ንጉሴ የስደተኞች የምግብ አቅርቦት ከሌላ ነገር ጋር የሚገናኝ አይደለም በማለት የተራድዖ ድርጅቶች በተለያየ ምክንያት ያቋረጡትን ድጋፍ እንዲያስቀጥሉ ጠይዋል።
 

ጋምቤላ የሰፈሩ የደቡብ ስደተኞችምስል picture-alliance/AA/W. Hailu

ኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት እና መሰል ችግሮች ከአገልግሎት ውጪ የሆኑትን ሳይጨምር በአሁኑ ጊዜ ስደተኞችን የሚያስተናግዱ 25 መጠለያ ጣቢያዎች መኖራቸውንም ነግረውናል። ርእሰ ከተማ አዲስ አበባ ውስጥም 80 ሺህ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች እንደሚኖሩ ኃላፊው ገልፀዋል።
ከስደተኞች ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ውስጥእስራኤል፣ ዩጋንዳ እና የአፍሪቃውያን ስደተኞች እጣ በተቋቋመው ኩመር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የኮሌራ ወረርሽኝ ተከስቶ ዘጠኝ ሱዳናውያን ስደተኞች እንደሞቱ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ከሰሞኑ አስታውቋል፡፡
ኢሰመኮ በበኩሉ በጋምቤላ 30 ስደተኞች መሞታቸውን አስታውቋል። በአማራ ክልል በቅርቡ ከተቋቋመውና ኤርትራዊያን ስደተኞች ከተጠለሉበት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የድጋፍ አቅርቦትን የተመለከተ ቅሬታ እየቀረበለት መሆኑን፣ ይሁንና ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በስፍራው ተገኝቶ ምልከታም ሆነ ክትትል ማድረግ እንዳልቻለ አስታውቋል።


ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW