1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት አለባት » የትግራይ ተቃዋሚዉ ፓርቲ - ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ

ዓርብ፣ መስከረም 2 2018

በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ የኢትዮጵያ መንግስት በቀይባህር ጉዳይ ዙርያ የያዘው አቋም እንደሚደግፍ አስታወቀ። ፓርቲው በትግራይ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ እንዲኖር የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር መድረክ ሊያመቻች ይገባል ብሏል። ፓርቲዉ 'የአባቶቻችን ርስት' ያለውን ቀይባህርን ማስመለስ ይገባዋል ብሏል።

መቀሌ ከተማ ፤ ትግራይ ክልል
መቀሌ ከተማ ፤ ትግራይ ክልል ምስል፦ Million Haileselassie/DW

ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ፥ ሕገወጥ የመሬት ወረራ በመቐለ እየተፈፀመ ነው አለ

This browser does not support the audio element.

በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ የኢትዮጵያ መንግስት በቀይባህር ጉዳይ ዙርያ የያዘው አቋም እንደሚደግፍ አስታወቀ። ፓርቲው በትግራይ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ እንዲኖር የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር መድረክ ሊያመቻች ይገባል ብሏል። በትግራይ በተቃዋሚነት ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሆነው ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ለመገናኛ ብዙሐን መግለጫ የሰጠ ሲሆን፥ በተለያዩ ጉዳዮችም ዙርያ አቋሙን አስታውቋል። ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ እንዳለው ኢትዮጵያ መንግስት በቀይባህር ጉዳይ ዙርያ የያዘውን አቋም እንደሚደግፍ ያስታወቀ ሲሆን፥ 'የአባቶቻችን ርስት' ያለው ቀይባህርን የሚቻሉ መንገዶች ሁሉ ተጠቅሞ ከሣላሳ ዓመት በፊት የተወሰደ ባህር የኢትዮጵያ መንግስት ማስመለስ ይገባዋል ብሏል። የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ዋና መስሪያ ቤትን የማስመረቅ አንድምታ?

የትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ህዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ አብርሃም ፅጌ ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት አለባት የሚለው እንደግፈዋለን። ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘት አለባት። በዚህ ሰላሳ ዓመት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ የተሰጠ ስለሆነና እንደሀገርም ሀገሪቱ አሁን ወደገባችበት አደጋ ያስገባ ስለሆነ ይህ ሊስተካከል ሊመለስ ይገባል። ባህሩ የኛ ነው የሚል እምነት አለን፣ እንዴት ይመለስ የሚለው ግን ሕጋዊ በሆነ፣ ሰላማዊ በሆነ እንዲሁም ህዝብ ወደ አደጋ በማያስገባ መንገድ መሆን ይገባዋል። ይህ ካልሆነ ግን የኢፊድሪ መንግስት የወሰነው የምንቀበል መሆኑ መግለፅ እንሻለን" ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከቅርብ ግዜ ወዲህ እያንፀባረቀው ባለው የባህር በር ማግኘት ጉዳይ የተለያዩ አስተያየቶች የሚሰጡ ሲሆን፥ በትግራይ ካሉ የፖለቲካ ሐይሎች መካከል ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ይህ አጀንዳ በግልፅ እንደሚደግፍ የገለፀ ቀዳሚ ፓርቲ ያደርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ ፖርቲው ህወሓት ከኤርትራ ጋር ያደርገዋል የሚባለው 'ፅምዶ' በሚባል የሚታወቅ ጥምረት ሕገወጥ በማለት አውግዟል። የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ያቀረበው ጥሪ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተቃዋሚው ፓርቲ ትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ በትግራይ ሐይሎች መካከል ያለው ክፍፍል አሳሳቢ መሆኑ፥ ግጭት ሳይፈጠር ሁሉም ሐይሎች መሳርያቸው አስቀምጠው ወደሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ጠይቋል። የትንሳኤ ሰብዓ እንደርታ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ አብርሃም ፅጌ "የትግራይ ህዝብ፣ በአጠቃላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጎዳ ስለሆነ ሁሉም ሰላማዊ የሆነ መንገድ ተከትለው እንዲጓዙ ጥሪ እናቀርባለን። አንድ የነበሩ አካላት ናቸው አሁን ላይ መልሰው ለህዝቡ መከራ ይዘው እየመጡ ያሉት። ስለዚህ ትጥቅ አስፈላጊ እንዳልሆነ በመገንዘብ፥ ግዚያዊ አስተዳደሩ ሰላማዊ መድረክ እንዲከፍት እንገፋለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW