ኢትዮጵያ፤ የፍርድ ሒደትና የመንግሥት ፊልሞች
ሐሙስ፣ የካቲት 14 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠረዉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፈዉ ጥር ሃያ-ስምንት ጀሐዳዊ ሐረካት በሚል ርዕሥ ያሰራጨዉ ፊልም የብዙዎችን ተቃዉሞ፥ የጥቂቶችን ቅሬታ፣ ጥያቄ አስከትሏል።ፊልሙ የተሰራጨዉ የፍርድ ቤት እግድን ጥሶ ነዉ መባሉ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ማስከበር የሚገባዉን የሐገሪቱን ሕገ-መንግሥት መጣሱን፥ የሕግ የበላይነት አለመከበሩን ያረጋግጣል የሚል ጠንካራ ትችት ገጥሞታል።ተቃዉሞ፥ ቅሬታ፥ ጥያቄዉ እና ትችቱ የሳምንቱ የዉይይት ርዕሳችን ነዉ።የሕግ ባለሙያዎችና ፖለቲከኞችን ጋብዘናል።
ነጋሽ መሐመድ