1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮ ቴሌኮም ስለ ኢንተርኔት ገደቡ ምን አለ?

ዓርብ፣ ሰኔ 16 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ የተጣለው የኢንተርኔት አገልግሎት ገደብ ከሥልጣኔ ውጪ ነው ሲል መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም ገልፀ ። የተቋሙ የበላይ ኃላፊ ይህንን ያሉት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ9 ወራት የሥራ እንቅስቃሴያቸውን ዘገባ ሲያቀርቡ ጥያቄ ከቀረበላቸው በኋላ ነው።

Frehiwot Tamru, CEO Ethio Telecom, in Addis Abeba, Ethiopia at Ethio Telecom
ምስል Hanna Demisie/DW

ከተሰጠው ሥልጣን ውጪ መሆኑን ገለጸ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ውስጥ የተጣለው የኢንተርኔት አገልግሎት ገደብ ከሥልጣኔ ውጪ ነው ሲል መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮም ገልፀ ። የተቋሙ የበላይ ኃላፊ ይህንን ያሉት ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የዘጠኝ ወራት የሥራ እንቅስቃሴያቸውን ዘገባ ሲያቀርቡ «ኢንተርኔት ለምን ይዘጋል?» የሚል ጥያቄ ከቀረበላቸው በኋላ ነው።

«ኢንተርኔት ለምን ይዘጋል?» የሚለው ጉዳይ መፍትሔ እንዲሰጠውና ደንበኞቻቸው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስሙን ያልጠቀሱት ከላይ ያሉት አካል ውሳኔውን እንዲቀልብስ ጥረት እንደሚያደርጉ ዋና ሥራ አሥፈፃሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ ገልፀዋል። 

በሌላ በኩል በፀጥታ መደፍረስ እና በጦርነት ምክንያት በሰባት ክልሎች ከፍተኛ ውድመት ደርሶባቸው የነበሩ ብዙ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ተጠግነው ዜጎች የቴሌኮም አገልግሎት መልሰው ማግኘት መቻላቸውን የገለፁት ፍሬሕይወት ትምሩ አሁንም ጥገና የሚያስፈልግልቸው በርካታ መሠረተ ልማቶች እንዳሉ ተናግረዋል። 

ጥገና ተደርጎላቸው ለአገልግሎት ለበቁ መሠረተ ልማቶች ከመንግሥትም ይሁን ከሌላ አካል የጥገና በጀት አለማግኘታቸውን እና በተቋሙ አቅም ብቻ መሸፈኑንም ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW