1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፍልሰትአፍሪቃ

ኢትዮ-ኬንያ የኤርትራዊያን አዲስ የፍልሰት መስመር

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሰኞ፣ መጋቢት 14 2018

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በመጠቀም በቱርካና ግዛት በኩል ወደ ኬኒያ የሚሻገሩ ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ፡፡ ባለፈው የ2017 ዓ.ም ብቻ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ኤርትራዊያን በዚሁ መስመር ለመውጣት ሲሞክሩ በፀጥታ ሀይሎች መያዛቸውን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ስደተኞቹ የተያዙት ኢትዮ ኬኒያን ድንበር በማቋረጥ በቱርካና በኩል ወደ ኬኒያ ግዛት ለመግባት ሲሞክሩ መሆኑ ተነግሯል።
ስደተኞቹ የተያዙት ኢትዮ ኬኒያን ድንበር በማቋረጥ በቱርካና በኩል ወደ ኬኒያ ግዛት ለመግባት ሲሞክሩ መሆኑ ተነግሯል።ምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

ኢትዮ-ኬንያ የኤርትራዊያን አዲስ የፍልሰት መስመር

This browser does not support the audio element.

በደቡብ ኢትዮጵያ በኩል በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኬኒያ ሲሻገሩ ደረስኩባቸው ያላቸውን 48 ኤርትራዊያንን በቁጥጥር ሥራ ማዋሉን የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስ አስታወቀ ፡፡ ኤርትራዊያን ፍልሰተኞቹ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ የተያዙት  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ውስጥ ነው ፡፡ፍልሰተኞቹ ሊያዙ የቻሉት ያለጉዞ ሰነድ የኤትዮ ኬኒያ ድንበርን ለማቋረጥ በሌሊት በመጓዝ ላይ እንዳሉ መሆኑን  ለዶቼ ቬለ  የተናገሩት የሐመር ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ኢንስፔክተር ጳውሎስ መቆያ “ ፍልሰተኞቹ ከሌሊቱ 9 ሰዓት በጭነት ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ እንዳሉ ነው የተያዙት ፡፡ ቁጥራቸው 48 ሲሆን አብዛኞቹ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ናቸው ፡፡ የተያዙት የኢትዮ ኬኒያን ድንበር በማቋረጥ በቱርካና በኩል ወደ ኬኒያ ግዛት ለመግባት ሲሞክሩ ነው “ ብለዋል  ፡፡

የፍልሰተኞቹ ገፊ ምክንያቶች

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በመጠቀም በቱርካና ግዛት በኩል ወደ ኬኒያ የሚሻገሩ ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ፡፡ ባለፈው የ2017 ዓ.ም ብቻ ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ ኤርትራዊያን በዚሁ መስመር ለመውጣት ሲሞክሩ በፀጥታ ሀይሎች መያዛቸውን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡

አቶ ዳንኤል መለሰ ንጋት ግሎባል ኢኒሼቲቭ የተባለ በፍልሰተኞችናከፍልሰት ተመላሽ ዜጎች ላይ የሚሠራ ግብረ ሠናይ  ድርጅት መሥራችና ዳይሬክተር ናቸው ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ ለመጣው ኤርትራዊያን ፈልሰተኞች ቁጥር መጨመር የተለያዩ ገፊ ምክንያቶች መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ ዳንኤል “ መቋጫ የሌለው የግዳጅ ውትድርና አንዱ ምክነያት ነው ፡፡ የፖለቲካና የኢኮኖሚው ሁኔታና የአካባቢው አለመረጋጋት ሌላው የፈልሰት መነሻ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡ እንዲሁም የተሻሻለው የኢትዮጵያ የፍልሰተኞች  አዋጅ ፍልሰተኞች እንደማንኛውም ዜጋ ኢትዮጵያ ውስጥ የመኖር መብትን የሚሰጥና በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስን ያስቀረ መሆኑ ለፍልሰት እና በመሸጋገሪያነት ለመጠቀም እንዲመርጡ አድርጓቸዋል “ ብለዋል ፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በመጠቀም በቱርካና ግዛት በኩል ወደ ኬኒያ የሚሻገሩ ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ፡፡ምስል፦ Shewangizaw Wegayoh/DW

ፍልሰተኞች ለምን የኢትዮ ኬኒያ ድንበርን ይመርጣሉ ?

ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች ወደ ተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለመሰደድ ኢትዮጵያን በመሸጋገሪነት እንደሚጠቀሙ ይታወቃል ፡፡ ለረጅም ጊዜ የሱዳን ፣ የጅቡቲ እና የሶማሌ ላንድ በሮችን በመውጫነት ሲጠቀሙ የቆዩ ቢሆንም  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን  አትዮ ኬኒያ  ተጨማሪ የፍልሰተኞች መስመር  እየሆነ ይገኛል ፡፡ የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምቦ መቃሳ ለዚህ የራሱ የሆነ ምክንያት አለው ይላሉ ፡፡

የኢትዮ ኬኒያ መስመር ከኬኒያ በተጨማሪ ወደ ዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ለመሸጋገር እንደሚያስችል የጠቀሱት አቶ አምቦ “ መስመሩ ከሌሎች የመውጫ በሮች ጋር ሲነጻጸር ብዙ የቁጥጥር ኬላዎች የማይበዙበት መሆኑ ይህን እንዲመርጡ አድርጓቸዋል፡፡ በተለይ ብዙ ኤርትራዊያን ፍልሰተኞች በዩጋንዳ የሚገኙ መሆናቸውና በቀላሉ በዛው ወደ ሌሎች አገራት ለማሸጋገር የሚያስችላቸው በመሆኑ ነው “ ብለዋል ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ 

ኂሩት መለሰ 

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW