ኢዜማ ለመንግሥት ያስተላለፈው ማሳሰቢያ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 6 2014
ማስታወቂያ
በብልጽግና ፓርቲ ባለሥልጣናት መካከል አደባባይ የወጣው ንትርክ ፓርቲው ራሱን አገራዊ እንደሆነ ቢገልጽም የብሔር ፓርቲ የመሆኑ ማሳያ እንደሆነና ይህም አገራዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( ኢዜማ ) አመለከተ። የብልጽግና አመራሮች እርስ በርስ እየተናከሱ ለአገር ሥጋት ሆነዋል ሲል ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ወቅሷል። የሀገሪቱን የጸጥታ ችግር ቅድመ ትንበያ የሚሰራው አካል ደካማ ወይም ቸልተኛ በመሆኑ የንጹሃን ዜጎች ሕይወት እንደዋዛ እንዲቀጠፍ ሀብትና ንብረትም እንዲወድምም አድርጓል ብሏል። ኢዜማ እንዳለው በአገሪቱ ከፍተኛ የመሬት ወረራ እየተፈፀመ ነው። ብልጽግና ለአምስት ዓመታት ልምራችሁ ሥልጣን ስጡኝ ካለ በኋላ ራሱ በአምስት ወራት ውስጥ ችግር ውስጥ ገብቷል ሲልም ኢዜማ ተናግሯል። ኢትዮጵያ አሁን ፈተና ውስጥ ትገኛለች ያለው ፓርቲው አገረ መንግሥቱ በፖለቲካ እንዝህላልነትና በአገሪቱ መሪዎች ትኩረት አለመስጠት ምክንያት ችግር ውስጥ ገብታለች ብሏል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ