ኢድ አልፈጥር በአዲስ አበባ እና ቃሊቲ
ረቡዕ፣ ሰኔ 29 2008ማስታወቂያ
ዘንድሮ የኢድ አልፈጥር በዓል ስነሥርዓት በአዲስ አበባ የጀመረው ታዳሚዎች ወደ ስታዲየም ገብተው ሳይጨርሱ ሲሆን፤ የተጠናቀቀውም በጊዜ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለም የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ በቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚገኙ ሙስሊም እስረኞችን የመጎብኘት ወይንም የመዘየር ስርዓት ተከናውኗል። በዓልን ብዙዎች በተለያየ መልክ ያከብራሉ። አንዳንዶች ከቤተሰብ፤ ከዘመድ አዝማድ ጋር በመሰባሰብ፤ ሌሎች ደግሞ ከወዳጆቻቸው ጋር በመገናኘት ያከብሩታል። አንዳንዶች ደግሞ የታመሙ ሰዎችን፤ አቅመ ደካሞችን፣ እስረኞችን በመጠየቅ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም በዓሉን ሲያከብሩ ይታያል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ/ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ