1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤልሳቤጥ ከበደ በመታወቂያ ዋስ ከእስር ተፈታለች

ዓርብ፣ ሚያዝያ 30 2012

ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚድያ አሰራጭታለች በሚል በቁጥጥር ስር ውላ ከአንድ ወር በላይ በእስር ላይ የቆየችው ኤልሳቤጥ ከበደ ትናንት በመታወቂያ ዋስ ከእስር ተፈታለች ፡፡

Göttin Justitia
ምስል picture-alliance/dpa/U. Baumgarten

ኤልሳቤጥ ከበደ ከእስር ተለቀቀች

This browser does not support the audio element.

ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚድያ አሰራጭታለች በሚል አዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ውላ ከአንድ ወር በላይ በሐረር ከተማ በእስር ላይ የቆየችው ኤልሳቤጥ ከበደ ትናንት በመታወቂያ ዋስ ከእስር ተፈታለች ፡፡ኤልሳቤጥ ለDW በስልክ በሰጠችው ምላሽ ቆይታዋም ሆነ የፍርድ ሂደቱ ህገመንግስታዊ ድንጋጌን የጠበቀ አልነበረም ብላለች፡፡የክልሉ ፍርድ ቤት ጉዳዯን ማየት እንደማይችል እና ነዋሪነቷ አዲስ አበባ ሆኖ ሳለ ወደ ሐረር መወሰዷ አግባብ አለመሆኑን ስትቃወም እንደነበር ገልፃ በመጨረሻ ክርክሩ ምላሽ አግኝቶ ክሷ ወደ አዲስ አበባ እንዲዞር መደረጉን ተናግራላች፡፡ትናንት ወደ አዲስ አበባ ተወስዳ በመታወቂያ ዋስትና የተለቀቀችው ኤልሳቤጥ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተወሰደው እርምት ተገቢ መሆኑን ጠቁማለች፡፡
መሳይ ተክሉ
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW