1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ኤርትራ በፕሬስ ነፃነት የዓለማችን መጨረሻ ናት ተባለ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2011

የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ በዓለማችን ምንም ለዉጥ ያላሳየች የመጨረሻዋ ሃገር ኤርትራ ናት ሲል ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ማኅበር አስታወቀ።  ማኅበሩ በቅርቡ በጀርመን መዲና በርሊን ላይ ይፋ ባደረገዉ ጥናት እንዳሳወቀዉ ፤ ኤርትራ ባለፉት 10 እና 15 ዓመታት በፕሬስ ነፃነት ላይ ምንም አይነት መሻሻልን አላሳየችም።

Aaron Berhane Professor aus Eritrea
ምስል፦ DW/Y. Hailemichael

ባለፉት 10 እና 15 ዓመታት ኤርትራ በፕሬስ ነፃነት ምንም መሻሻልአላሳየችም

This browser does not support the audio element.

የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ በዓለማችን ምንም ለዉጥ ያላሳየች የመጨረሻዋ ሃገር ኤርትራ ናት ሲል ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ማኅበር «Reporters Without Borders» አስታወቀ። ማኅበሩ በቅርቡ በጀርመን መዲና በርሊን ላይ ይፋ ባደረገዉ ጥናት እንዳሳወቀዉ ፤ ኤርትራ ባለፉት 10 እና 15 ዓመታት በፕሬስ ነፃነት ላይ ምንም አይነት መሻሻልን አላሳየችም። አሁንም ለዓመታት የታሰሩት ጋዜጠኞች  አልተፈቱም፤ ቤተ-ዘመዶቻቸዉም የታሰሩበትን ቦታ አያዉቁም። ወጣት የሆነዉ አብዛኛዉ የማኅበረሰብ ክፍል በብሔራዊ ዉትድና ተጠምዶአል፤  በ 21 ኛዉ ክፍለ ዘመን የሃሳብ እና የመረጃ መለዋወጫ የሆነዉን የኤሌክትሮኒክስና የኢንተርኔት ተጠቃሚ አይደለም። የዓመቱ የሚከበረዉ የፕሬስ ነፃነት ቀን የፊታችን አርብ በመላዉ ዓለም ታስቦ ይዉላል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል

 አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW