1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራ፣ የምግብ እጥረት እና የመስኖው ፕሮዤ

ሰኞ፣ ጥቅምት 4 2006

በዓለም የምግብ እጥረት የሚታይባቸው አካባቢዎች መዘርዝር ሰንጠረዥ ዛሬ ይፋ ሆኗል። ኤርትራ ዘንድሮም ብዙ ሕዝብ በቂ ምግብ ከማያገኙባቸው ሀገራት መካከል ትቆጠራለች።

TO GO WITH AFP STORY BY PETER MARTELL A shepherd rests in the shade in the Eritrean Red Sea village of Hirgigo on November 17, 2007. The seed-planting is part of a remarkable yet low-tech pilot project, designed as a model to improve the lives of desert coastal communities by using the salt-water trees to increase fish numbers, provide feed to raise livestock - and combat desertification. At Hirgigo, research into planting mangroves began a decade ago, challenging conventional wisdom that the saltwater plants also needed fresh water to grow -- a major limitation in the arid regions where the trees are needed most. AFP PHOTO / Peter MARTELL (Photo credit should read PETER MARTELL/AFP/Getty Images)
ምስል PETER MARTELL/AFP/Getty Images

ትልቁ የህዝቧ ከፊል በግብርና የሚተዳደርባት ኤርትራ በሚገጠማት ድርቅ የተነሳ ሰብል ስለማይሰበሰብ ብዙዎች ለረሀብ ይጋለጣሉ። የኤርትራ መንግስት በመስኖው አውታር ችግሩን ለማስወገድ ቢጥርም እስካሁን ስኬታማ እንዳልሆነ ነው የዶይቸ ቬለዋ አንትየ ዲካንስ የፃፈችው ዘገባ የሚያሳየው።

ጥቂት ህፃናት ውሃ ውስጥ ይንቦጫረቃሉ። በሌላኛው የሀይቅ ጫፍ ከብቶች ውሃ ይጠጣሉ። በደቡብ ኤርትራ መሀንዲሶች ለመስኖ ስራ ብለው የሰሩት ሀይቅ ነው። በዚህ አካባቢ ያሉ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በድርቅ ይጎዳሉ። ስለሆነም በዝናብ ወቅት በተቻለን መጠን ብዙ ውሃ ለማጠራቀም እንሞክራለን ይላሉ የፕሮጀክቱ ኃላፊ ስምዖን አብርሃ፤ « እንደዚህ ዓይነት ግድብ ለመስራት ሁለት ወራት ብቻ ነው የሚወስድብን። የመንደሩ ሰው ሁሉ እና እንሰሶች በውሃው ሊጠቀሙ ይችላሉ። ለመስኖ መጠቀም የሚፈቀድላቸው ግን ገበሬዎች ብቻ ሲሆኑ፣ ብዙዎቹ ሴቶች ብቻ ናቸው። በዓመት ሶስት ጊዜ ለማምረት እንዲችሉ ማድረግ ነው ዓላማው። »

ኤርትራ ውስጥ አብዛኛው ህዝብ የሚተዳደረው በግብርና ነው። ሰዎቹ ማሽላ፣ በቆሎ እና አትዕክልት ያመርታሉ። ዝናብ ካልዘነበ ግን ምንም አይነት ምርት አይኖርም። በዚህም የተነሳ ነው ኤርትራ በየዓመቱ በሚወጣው የዓለም አቀፍ ሰንጠረዥ ውስጥ ችግሩ አሳሳቢ ከሆነባቸው ሀገራት መደዳ የምትቀመጠው። መሀንዲሱ አቶ ስምዖን ሰው ሰራሹ ግድብ ለዚህ ችግር መፍትሄ እንደሚያገኝ ባለሙሉ ተስፋ ናቸው። « ሰዎቹ ለእንስሶቻቸው ሳይቀር ምግብ ማግኘት ችለዋል። ልጆቻቸውን የሚያበሉት በቂ ምግብ አላቸው። የተረፋቸውን ወደ አስመራ ሳይቀር ይሸጣሉ። »

ይህ የመስኖ አውታር የተተከለው ከህንድ መንግስት በተወሰደ ብድር ነው። የአውሮፓ ህብረትም በተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ይሳተፋል። ይሁንና ይህንን ድጋፍ ማቅረቡ አዳጋች እየሆነ ነው የተገኘው። ምክንያቱም የኤርትራ መንግስት ሀገሪቱን ለውጭው ዓለም ከመዝጋቱም ሌላ። የረሃብም ሆነ የድርቅ ችግር እንደሌለ ነው የሚናገረው። አትሞ

ማሳቸውን በመኮተኮት ላይ የነበሩት እና መሀንዲሱ የሚያብራሩትን በጥንቃቄ ይሰሙ የነበሩት ገበሬዋ ስምረት አርአያ ከዚህ የተለየ አስተያየት ነው ያላቸው። « በኤሌክትሪክ ኋይል ነው የሚሰራው። ገበሬዎቹ ነዳጅም ይሁን ሌላ የኃይል ምንጭ መግዛት አይችሉም። »ለነገሩ መስኖው ካላንዳች ችግር መስራት ነበረበት፣ ግን ገበሬዋ ደስተኛ አይደሉም።

« በኤልክትሪክ ኃይል ስለሚሰራ በሳምንት አንዴ ነው ውሃ የምናገኘው። ኮሬንቲ ከሌለ ደግሞ የውሃ ማውጫው አይሰራም። » ውዱ መሳሪያ እስካሁን ያስገኘው ፋይዳ የለም። የኤልክትሪኩ ኃይል ከስንት አንዴ ነው የሚሰራው። መብራት ከሌለ ውሃም የለም ማለት ነው። ገበሬዋ እስካሁን በአመት አንዴ ብቻ ምርታቸውን እንደሰበሰቡ ይናገራሉ። አራት ጆንያ በቆሎ ነበር። ይህንንም ሸጠው ወደ 2500 ብር ግድም ነው ያገኙት። ለገበሬዋ እና ለልጆቻቸው ከዚህ የተገኘው ገቢ በቂ አይደለም።

«ብዙ ወጪ ስላሉን ምንም ያህል ትርፍ አናገኝም። ለምሳሌ ግብር እንከፍላለን። በዛ ላይ እርሻችንን ለሚጠብቁት ኃይላት እንከፍላለን።» የመስኖ ስራው እስካሁን አካባቢውን ወደፊት አላራመደም። ዝናብ ካልዘነበም ያካባቢው ገበሬዎች እንደገና በምግብ እጦት መሰቃየታቸውና መራባቸው አይቀርም።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW