ኤኮዋስ የት ነዉ?
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 27 2014![Symbolbild | ECOWAS | Westafrikanischer Regionalblock verabschiedet neuen Plan zur Einführung einer einheitlichen Währung im Jahr 2027](https://static.dw.com/image/57970216_800.webp)
ማስታወቂያ
ጠመንጃ ያነገቡ ወጣት የጦር መኮንኖች እና ራሳቸውን የነጻ አውጪ ድርጅት ብለው የሚጠሩ ቡድኖች አፍሪቃ ውስጥ በተደጋጋሚ ሥልጣን በኃይል ሲቆጣጠሩ ይታያል። እነዚህ ከፖለቲካው መድረክ ለጊዜው ድምፅ አጥፍተው የቆዩ ኃይላት ዳግም ብቅ ብለው በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት በተለይም በምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት መንግሥት ገልብጠው ሥልጣን በኃይል ይዘዋል። የምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የኤኮኖሚ ማኅበረሰብ (ECOWAS) ሥልጣን በኃይ የያዙትን በኤኮኖሚም መነጠል ያስፈልጋል ተብሏል። በተጨባጭ የሚታይ ነገር ግን የለም። እናም የፖለቲካ ተንታኞች ኤኮዋስ ከወዴት ይሆን ያለው የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ሃገራት ሥልጣን በኃይ የሚይዙት ላይ በጋራ መልስ መስጠት እና መመከት ያስፈልጋቸዋልም ተብሏል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሰለሞን ሙጬ