1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እምሩ ዘለቀ በጀርመን የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ አምባሳደር

ሐሙስ፣ ኅዳር 8 2015

አምባሳደር እምሩ ዘለቀ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ከአራት አስርተ ዓመታት በላይ በስደት በዩናይትድ ስቴትስ የኖሩት የዘጠና ዘጠኝ ዓመት የዕድሜ ባለጸጋዉ አምባሳደር እምሩ ዘለቀ፤ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን በጀርመን የመጀመርያዉ አምባሳደር፤ በፈረንሳይ፤ በጋናና በእስካንዴንቪያ ሀገራትም አምባሳደር ሆነዉ አገልግለዋል።

Erster Botschafter von Äthiopien in Deutschland Imru Zelleke gestorben

አምባሳደር እምሩ ዘለቀ የ 99 ዓመት እድሜ ባለፀጋ ነበሩ

This browser does not support the audio element.

 

አምባሳደር እምሩ ዘለቀ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።  ስለ አምባሳደር እምሩ ዘለቀ የነገሩን ልጅ ልዕልት አደይ እምሩ ናቸዉ። ከአራት አስርተ ዓመታት በላይ በስደት በዩናይትድ ስቴትስ የኖሩት የዘጠና ዘጠኝ ዓመት የዕድሜ ባለጸጋዉ አምባሳደር እምሩ ዘለቀ፤ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን በጀርመን የመጀመርያዉ አምባሳደር ሆነዉ አገልግለዋል። በፈረንሳይ፤ በጋናና በእስካንዴንቪያ ሀገራትም አምባሳደር ነበሩ። በዩናይትድ ስቴትስ ዎል እስትሬት፤ በኬሚካል ባንክ ውስጥ የአፍሪቃ ምክትል ፕሬዚደንትና የልዩ ልዩ ኩባንያዎች የንግድ አማካሪም ሆነዉ ሰርተዋል። ጣሊያን በተለይ በአዲስ አበባ ላይ ከ30ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን በጨፈጨፈበት ወቅት ሁኔታውን በቅርበት ዓይን የተመለከቱ እና ስለሁኔታውም የጻፉ ኢትዮጵያዊም ናቸው። የአምባሳደር እምሩ የመጀመርያ ልጅ ልዕልት አደይ እምሩ። ለቀብር የአባታቸዉን አስክሬን ወደ አዲስ አበባ ይዘዉ ከመነሳታቸዉ በፊት ከዩናይትድ ስቴትስ በስልክ ስለአባታቸዉ የህይወት ጉዞ በደስታ በሙሉ ፍላጎት አጫዉተዉናል። እኔና እህቴ አባታችንን ወደ ኢትዮጵያ ይዘነዉ እንሄዳለን ሲሉም ነዉ በሃዘኔታ የነገሩን። 

ምስል privat

የአፄ ኃይለስላሴን የልጅ ልጅ፤ ማለትም የልዑል መኮንን ልጅ፤ የሟቹ የልዑል ዳዊት መኮንን ባለቤት የሆኑት ልዕልት አደይ እምሩ እንደነገሩን፤ ከሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያ በምዕራብ ጀርመን ቦን ከተማ ኤምባሲዋን ስትከፍት አባታቸዉ እምሩ ዘለቀ የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነዉ በር የከፈቱ ናቸዉ። አምባሳደር እምሩ ዘለቀ ለሁለት ዓመታት በምዕራብ ጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነዉ ካገለገሉ በኋላም ወደ ሃገራቸዉ ተመልሰዉ ፤ በሃገር ቤት ለጥቂት ጊዜ ንግድ ላይ ተሰማርተዉ ነበር። ብዙም ሳይቆዩ በድጋሚ በመንግሥት ሥራ ላይ ተሰማሩ።  

ምስል privat

ልዕልት አደይ አባትዎ በጀርመን ቦን ከተማ የመጀመርያዉን የኢትዮጵያ ኤንባሲ መክፈታቸዉን ነግረዉኛል። ይህ ደሞ ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ መሆኑ ነዉ። ልዕልት አደይ እንደሚሉት የአፄ ኃይለሥላሴ አስተዳደር በወታደራዊዉ ደርግ ከወደቀና ደርግ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ በመጀመርያዉ ዓመት አምባሳደር እምሩ ስራ  ላይ ነበሩ። 

ምስል privat

አምባሰደር እምሩ ዘመዴ ናቸዉ ከዝያም በላይ አማካሪዬ ነበሩ ያሉን የጀርመን የአፍሪቃ እና የመካከለኛዉ ምስራቅ ጉዳዮች አማካሪ እንዲሁም የታሪክ ምሁርና በጀርመን ታዋቂ ደራሲ ልዑል ዶ/ር አስፋ ወሰን አስራተ አምባሳደር እምሩ ሃገራቸዉን ወዳጅ እንደነበሩ ይናገራሉ።

ልዑል አስፋወሰን ስለዲፕሎማሲ አንስተዋል አምባሳደር እምሩ ዘለቀ በጀርመን የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነበሩ፤ እስቲ ይንገሩን ስለታሪኩ ልዑል አስፋ ወሰን ምናልባት ፤ ሌላ ስለአምባሳደር እምሩ የሚነግሩን ነገር ካለ ? ያልነሳነዉ ነገር። ጥቅምት 11 ቀን በተወለዱ በ99 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ለእዉቁ አምባሳደር እምሩ ዘለቀ ባለፈዉ ቅዳሜ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የፍትሃትና የፀሎት ሽኝት መረሃግብር ተካሂዷል። የአምባሳደር እምሩ ዘለቀ ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓም በተወለዱባት በአዲስ አበባ ከተማ ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን አፅም ባረፈበት ቦታ ላይ ቤተሰቦቻቸዉ ወዳጆቻቸዉ በተገኙበት ስርዓተ ቀብራቸዉ ተፈፅሟል። 

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW