እሥራኤልና ጋዛ፣
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 2001ማስታወቂያ
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማኑቸር ሞታኪ፣ እሥራኤል ጋዛና ስትደበድብ ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምንም አላደረገም በማለት በጥባቅ ነቀፉ። የዮርዳኖስ ንጉሥ አብደላና ፍልስጤማዊቷ ባልተቤታቸው ንግሥት ራኒያ፣ በዚህ ሳምንት ከፍልስጤማውያን ጎን መቆማቸውን ለማሳየት ሁለቱም ደም ሰጥተዋል። በመዲናይቱ፣ በአማን 5 ሺ የሚሆኑ ፍልስጤማውያንና ዮርዳኖሳውያን ሰላማዊ ሰልፍ ካሳዩ በኋላ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር የተሰኘው ቡድን ባሳሰበው መሠረት ጂሃድ(ቅዱስ ጦርነት) እንዲካሄድ ሲሉ መጠየቃጨው ተገልጿል። በኢስታንቡል፣ ቱርክ፣ 5 ሺ ያህል ሰዎች አደባባይ ወጥተው እሥራኤልን አውግዘዋል። ከአሥራኤል በኩል፣ ዘጋቢአችን፣ ዜናነህ መኮንን Jerusalem Post የተባለውን የእሥራኤል ጋዜጣ በመጥቀስ ከኢራን ፣ በየመንና ኤርትራ በኩል ቻይና -ሠራሽ ጦር መሣሪያ ጋዛ ገብቷል ሲል ጠቅሷል። የዜናነህ ዝርዝር ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።