1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በድርቅና ረሃብ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ የማሰባሰቢያ ዘመቻ

ልደት አበበ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 5 2016

በዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደርም በድርቅና ረሃብ ለተጎዱ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረስ እንዲቻል በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅስቀሳ እና የገንዘብ ማሰባሰብያ ዘመቻ መጀመሩን ዶቼ ቬለ ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች ተረድቷል።

 የደረቀ የበቆሎ ማሳ
በአማሮም በተከሰተ ድርቅ የደረቀ የበቆሎ ማሳምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

በድርቅና ረሃብ የተጎዱ ኢትዮጵያውያን

This browser does not support the audio element.

በትግራይ ክልል ለረሀብ የተጋለጡ ዜጎች ለማገዝ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች፣ እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማትን ያካተተ አስቸኳይ ምላሽ ለትግራይ የተባለ ኮሚቴ መስርቶ ገቢ ማሰባሰብ መጀመሩ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርም በድርቅና ረሃብ ለተጎዱ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረስ እንዲቻል በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅስቀሳ እና የገንዘብ ማሰባሰብያ ዘመቻ መጀመሩን ዶቼ ቬለ ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች ተረድቷል።

ይህንኑ ለማስተባበር ከሚንቀሳቀሱት መካከል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዋግኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጻጻስ አቡነ በርናባስ ስላለው ሁኔታ እንዲህ ይላሉ። «እንደሚታወቀው በዚህ ሁለት ሶስት አመታት በጦርነት የተጎዳ አካባቢ ነው። ብዙ ዓብያተ ቤተክርስትያናት እንደፈረሱ እና ሳይሰሩ ያሉበት ሁኔታ እንዳለ ዜና ሳይሰሩ የቀረበት ሁኔታ አለ። አሁንም ቢሆን ሀገሪቱ ከጦርነት አልወጣችም»  ብለዋል። 

ይህ እንዳለ ሆኖ የ2015 ዓ,ም የመኸር ዝናብ ባለመዝነቡ በተለይም በስሀላ፣ ዝቋላ እና አበርገሌ ወረዳዎች እና ስድስት ቀበሌዎች ድርቅ መከሰቱን ያስረዳሉ።

በዋግህምራ ሁለት ወረዳዎች «ሰሚ አጥተዋል» መባሉ

ባለው ድርቅ እና ርሀብ ምክንያትም እስካሁን 13 ሰዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶች  በእነዚህ ወረዳዎች መሞታቸውንም  በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጻጻስ አቡነ በርናባስ ይናገራሉ። 

«4200 የወንድ ከብቶች ሞተዋል። ፍየል እና በግን ሳይጨምር ። ወደ 170 ሺህ የቀንድ ከብት ወደ ሌላ ቦታዎች ተሰደዋል። » ይላሉ። ችግሩም ዕለት ከዕለት እየተባባሰ ነው የመጣውም ይላሉ። ስለዚህም ችግር ኢትዮጵያውያን ወገኖች እንዲሰሙት እና በርሀብ ለተጎዱት ወገኖች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ እና ጎ ፈንድ ሚ መከፈቱን ያስረዳሉ።

«የሀገረ ስብከቱ አካውንም አለ። ጎ ፈንድ ሚም ተከፍቷል።  በዚህ በከፈትነው አካውንት ላይ በሁሉም ዓለም ያለ ህዝብ ሁሉ የተቻለውን ድጋፍ እንዲያደርግ። እዛም ያሉ ወገኖች እህል በመሸመት እና ወደ ቦታው እንዲያደርስ » በማድረግ ቢተባበር ሲሉ ጥሪ ያደርጋሉ። ገንዘቡም አሁን ለጠቀሷቸው ሶስት ወረዳዎች እንደሚውል በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጻጻስ አቡነ በርናባስ ተናግረዋል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW