1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታስረው እስካሁን ያልተለቀቁት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ

ረቡዕ፣ ጥር 25 2014

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ታስረው እስካሁን ያልተለቀቁት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ

Symbolfoto Justitia
ምስል picture alliance

በቀጣይ መሠራት ስለሚገባቸው ሥራዎች መግባባት ላይ ተደርሷል ተብሏል

This browser does not support the audio element.

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ታስረው እስካሁን ያልተለቀቁት በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ።ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫና ለDW በሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ እንዳለው ያልተለቀቁ ታሳሪዎች ጉዳያቸው በመደበኛ የፍርድ ሂደት እንዲታይና በ24 ሰአታት ፍርድ ቤት የመቅረብ መብታቸው እንዲከበር ጠይቋል። በኮሚሽኑ የሰብዓዊ መብቶች ምርመራና ክትትል ዳይሬክተር አቶ ኢማጅ አብዱልፈታህ ለDW ተጨማሪ ማብራሪያየሚኒስትርች ምክርቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑ በበጎ ጎኑ እንደተመለከተው ያተተው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤትም ወሳኔውን ተቀብሎ እንደሚያጸድቀው ተስፋ እናደርጋለን ብሏል።

ከዚህ ጎን ለጎን የእስረኞች ሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ በጂማ፣ ሃዋሳና ድሬዳዋ ከተሞች ከሚመለከታቸው የፖሊስና የማረሚያቤት ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ምክክር መደረጉንም አክለዋል በምከከር መድረኩ በእስረኞች ሰብአዊ መብት አያያዝ የታዩ ክፍተቶች አስመልክተው አቶ ኢማጅ ለምሳሌ በኦሮሚያ በሚገኙ ስድስት ዞኖች ውስጥ በ10 ማረሚያ ቤቶች ላይ ኮሚሽኑ ያደረገው ክትትል ግኝቶች ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ገልጸው በማረሚያ ቤቶች  በተለይም  የታራሚ የይቅርታ አሰጣጥ መቆሙ፣ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው እስረኞች የቅጣት አፈጻጸም ላይ የታዩ ክፍተቶች፣ የማረሚያ ቤቶች የታራሚ መረጃ አያያዝ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አለመሆን፣ ከሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር  ያለው ችግር ሳይቀረፍ መቀጠሉ፣ በማረሚያ ቤቶች ልዩ ድጋፍ ለሚፈልጉ ታራሚዎች ሁኔታዎች አለመመቻቸታቸው፣ ከሚመለከታቸው ውይይት ተደርጎባቸው በቀጣይ መሰራት የሚገባቸው ስራዎች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል ሲሉ አክሏል፡፡
የሰብዓዊ መብት አያያዝ ለኮሚሽኑ ብቻ የሚወረወር ሰራ እንዳይደለ የገለጹት አቶ ኢማጅ የሚመለከታቸው ሃላፊዎችና ህዝቡ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW