እስራኤልና ጥብቁ የስደተኞች አመራር ዘይቤዋ
ሰኞ፣ ግንቦት 27 2004ማስታወቂያ
አንዳንድ የመንግሥት አባላት በሚሰነዝሯቸው የስደተኞችን መብዛት የማጥላላት ንግግርም ሳቢያ፤ በስደተኞች ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ቀጥሏል። ዛሬ ጧት፣ ኢየሩሳሌም ውስጥ፣ 18 የኤርትራ ተወላጆች በሚገኙበት በአንድ አሮጌ ባለ 2 ፎቅ ህንጻ ላይ ሆን ተብሎ በተወሰደ የማቃጠል እርምጃ 4 ኤርትራውያን የመቁሰልና በጢስ የመታፈን አደጋ ደርሶባቸው ወደ ሀኪም ቤት መወሰዳቸው ተነግሯል። እሥራኤል ለምንድን ነው በስደተኞች ላይ ጠጣር እርምጃ የምትወስደው? ፤ በዚያው በእሥራኤል ፣ የመንግሥት ያልሆነውን ፤ የአፍሪቃ ስደተኞች የዕድገት ማዕከል የተሰኘውን ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ባዩን ወደ እስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ አነጋግሬአቸው ነበር።
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ