1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ውዝግቦችአፍሪቃ

እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሦስት ሳምንት ማራዘማቸው

አበበ ፈለቀ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 16 2018

ካለፈው የካቲት አጋማሽ አንስቶ እስራኤል በኢራን ላይ የጋራ ጥቃት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስራኤል በሊባኖስ፣ በተለይም በደቡብ እና በዋና ከተማዋ ቤሩት ላይ የአየር ድብደባ ስትፈጽም ቆይታለች።

በደቡባዊ ሊባኖስ የተፈጸመው ድብደባ
በደቡባዊ ሊባኖስ የተፈጸመው ድብደባ (ፎቶ ከማኅደር)ምስል፦ Gil Eliyahu/REUTERS

እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሦስት ሳምንት ማራዘማቸው

This browser does not support the audio element.

 

እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በሦስት ሳምንታት ለማራዘም ተስማምተዋል ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሳውቀዋል። ስምምነቱ የመጣው የእስራኤል እና የሊባኖስ ባለሥልጣናት ዋይት ሀውስ ውስጥ ያልተለመደ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ እንደሆነ ተገልጿል። በሌላ በኩል በመካከለኛው ም|ሥራቅ የቀጠለውን ውዝግብና ውጥረት ለማርገብ ፓኪስታን የጀመረቸው የሰላም ድርድርን ቀጥላበታለች። በዛሬው ዕለትም የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወደ ፓኪስታን መጓዛቸው ተሰምቷል።

የመካከለኛው ምሥራቅ ውዝግብ ባያባራም የተኩስ አቁም ስምምነቶች ስለመራዘማቸውና የዓለም ኤኮኖሚ ባናጋው የሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ስለቀጠለው ውጥረት የዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀን ወደ ስቱዲዮ ከመግባታችን አስቀድሞ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW