1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

እስራኤል የቤተ እስራኤላውያንን የፍልሰተኞችን ፖሊሲ ልታሻሽል ነው

ሐሙስ፣ ነሐሴ 11 2015

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ እስራኤል ቤተእስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ የማስወጣት ፖሊሲዋን ልትከልስ እንደምትችል የሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ሚኒስቴር ዐስታውቋል። የእስራኤል መንግስት ውሳኔ የተሰማው ከአማራ ክልል ተጨማሪ ቤተእስራኤላውያንን የማስወጣት ዕቅድ እንደሌለ ማሳወቁን ተከትሎ ቤተእስራኤላውያን ለተቃውሞ አዳበባይ ከወጡ በኋላ ነው።

ቤተእስራኤላውያን እስራኤል ሲደርሱ
ከኢትዮጵያ የተነሱ ቤተ እስራኤላውያን እስራል ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ፎቶ ማህደር ምስል፦ Jack Guez/AFP/Getty Images

እስራኤል ከቤተእስራኤላውያን አንጻር የምትከተለውን ፖሊሲ ማሻሻል ለምን አስፈለጋት ?

This browser does not support the audio element.

በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ እስራኤል ቤተእስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ የማስወጣት ፖሊሲዋን ልትከልስ እንደምትችል የሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ሚኒስቴር ዐስታውቋል። የእስራኤል መንግስት ውሳኔ የተሰማው ከአማራ ክልል ተጨማሪ ቤተእስራኤላውያንን የማስወጣት ዕቅድ እንደሌለ ማሳወቁን ተከትሎ ቤተእስራኤላውያን ለተቃውሞ አዳበባይ ከወጡ አንድ ቀን በኋላ ነው። እስራኤል ባለፈው ሳምንት በአይሁዶች እና ተመላሽ ዘመዶቻቸው ህግ ወደ እስራኤል ለመመለስ ብቁ ናቸው ያለቻቸውን 204 ሰዎች ከጎንደር አስወጥታለች። እስራኤል ከ200 በላይ የሚሆኑ ዜጎቿን ከአማራ ክልል አወጣችሊከለስ ይችላል የተባለው የሀገሪቱ የፍልሰተኞች ፖሊሲ ተጨማሪ ቤተእስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ ለማውጣት እንደሚያግዝ ተገልጿል። ቤተእስራኤላውያኑ ባለፈው እሁድ ኢየሩሳሌም ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወገኖቻቸው እንዲመጡ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው ነበር። በሰልፉ ኢትዮጵያ አማራ ክልል ውስጥ እየተደረገ ያለው ጦርነት በክልሉ በሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያን ደህንነት ያሰጋናል ብለዋል። ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ደጅ በተደረገ ሰልፍ 204 ስደተኞች ከጎንደር እንዲወጡ መደረጉ ይታወሳል። የቤተ እስራኤላውያኑ ዘመዶቻቸው ከኢትዮጵያ እንዲወጡ የሚጠይቀው ሰልፍ ሲያደርጉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ የመጀመሪያው ነው።የእስራኤል መንግሥት ምስረታ 75ኛ ዓመት በሌላ በኩል እስራኤል በሱዳን እና ሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት እየተደረጉ ያሉ ጦርነቶችን ተከትሎ ተግባራዊ እያደረገች ያለው  ጥብቅ የስደተኞች ፖሊሲ ባለበት ይቀጥላል ነው የተባለው። እስራኤል በሱዳን በአጠቃላይ ፣ በምዕራባዊ ዳርፉር  የሚደረጉ ጦርነቶች ፣ እንዲሁም ከቱኒዚያ ፣ ሊቢያ እና ሌሎች ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ጠበቅ ያለ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ተጠቁሟል።

የእስራኤል መንግስት ውሳኔ የተሰማው ከአማራ ክልል ተጨማሪ ቤተእስራኤላውያንን የማስወጣት ዕቅድ እንደሌለ ማሳወቁን ተከትሎ ቤተእስራኤላውያን ለተቃውሞ አዳበባይ ከወጡ በኋላ ነው። ፎቶ ከማህደር፤ የእስራኤል መንግስት ምስረታ 75ኛ ዓመት ሲከበር ምስል፦ Eyal Warshavsky/SOPA Images via ZUMA Press Wire/picture alliance

ዜናነህ መኮንን 

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW