1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«እስከ ጊዜዉ በርቺ» አለማየሁ እሸቴ

ሐሙስ፣ መጋቢት 17 2007

«የዘፈኑን ዕድሜ ስነግራችሁ ሸመገለ እንዳትሉኝ እንጂ « ተማር ልጄ» የተዘፈነዉ የዛሬ ሰላሳ አምስት ዓመት ነዉ። ያዘለዉ መልክት እዉነተኛ አባት ለልጁ የሚሰጠዉ ምክር ነዉ። የሰዉ ልጅ ካልተማረ ዋጋ የለዉም። ስለሆነም አባቶች የሚሰጡንን ምክር በዚህ ዘፈን ለመጭዉ ትዉልድ የዘራሁት ነዉ ብዬ ነዉ የማምነዉ»

በጀርመንዋ መዲና በርሊን ላይ የሚገኘዉን አንጋፋዉ ድምፃዊ የአለማየሁ እሸቴን ነዉ ያደመጥ ነዉ። ጤናይስጥልኝ አድማጮች እንደምን አመሻችሁ። ድምፃጻዊ አለማየሁ እሸቴ በጀርመናዉያን የሙዚቃ ባንድ በመታጀብ ቀደም ሲል ያዜማቸዉን ሙዚቃዎች በማቅረብ ለጀርመናዉያን መገናኛ ብዙኃን ማብራርያ ሲሰጥ ነበር ያደመጥነዉ። መቀመጫዉን በርሊን ላይ ያደረገዉ «የሊስትሮ ማኅበር» የተሰኘዉ ድርጅት «እስከ ጊዜዉ በርቺ» የተሰኘዉን የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴን ሙዚቃ መሪ ቃሉ በማድረግና በእንግሊዘኛ «STAY STRONG UNTILL A BRIGHT DAY COMES» የሚለዉን ትርጉም በማስቀመጥ አንጋፋዉ ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴን ላበረከተዉ ሥራ እዉቅና ለመስጠት ለጥበቡ ክብር ለመሥጠት እንዲሁም ሙዚቃዎቹን በማስተዋወቅ አዳዲስ ሙዚቃዉንም ለሙዚቃ አፍቃሪዎች ጆሮ ለማድረስ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW