1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነ

Azeb Tadesse Hahn
ሐሙስ፣ መጋቢት 25 2017

ድምፀ-መረዋዉ አስቻለዉ ፈጠነ ይሉታል አድማጮቹ እና ተከታዮቹ። የከያኒ አስቻዉ ፈጠነ ሙዚቃዎች በተለይ እናትዋ ጎንደር የተባለዉ ሙዚቃዉ በዩቲዩብ በብዛት ከታዩ የኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች መዘርዝር መካከል ቀዳሚዉ ደረጃ ላይ ይገኛል። አስቻለዉ ፈጠነ ካዜማቸዉ እና የብዙዎችን ቀልብ ከሳቡት ሙዚቃዎቹ መካከል «አሞራዉ ካሞራ» ሲል ያዜመዉ አንዱ ነዉ።

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነ
«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነምስል፦ Aschalew Fetene

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነ

This browser does not support the audio element.

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነ

እቴ ወይ ልዋል -    ከደረትሽ መሐል፤

ናፈቀችኝ ጎንደር - የነአሞራዉ አገር፤ ሲል ያንጎራጎረዉ ፤ አርቲስት አስቻለዉ ፈጠነ ነዉ።

ድምፀ-መረዋዉ አስቻለዉ ፈጠነ ይሉታል አድማጮቹ እና ተከታዮቹ። የከያኒ አስቻዉ ፈጠነ ሙዚቃዎች በተለይ እናትዋ ጎንደር የተባለዉ ሙዚቃዉ በዩቲዩብ በብዛት ከታዩ የኢትዮጵያ ምርጥ ሙዚቃዎች መዘርዝር መካከል ቀዳሚዉ ደረጃ ላይ ይገኛል። በታሪክ ትምህርት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀዉ፤ አስቻለዉ ፈጠነ በቅጽል መታወቅያዉ (አርዲ) ካዜማቸዉ እና የብዙዎችን ቀልብ ከሳቡት ሙዚቃዎቹ መካከል «አሞራዉ ካሞራ» ሲል ያዜመዉ አንዱ ነዉ። አሞራዉ ካሞራዉ የተሰኘዉ ዘፈን የከያኒ አስቻለዉ ፈጠነ እንዳለዉ በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ተመልካች ተከታትለዉታል አልያም አድምጠዉታል። «እናትዋ ጎንደር» የተባለዉ ሙዚቃ ደግሞ ከ 20 ሚሊዮን  በላይ ተመልካቾች በዩትዩብ ላይ እንደተከታተሉት መዘርዝሩ ያሳያል። ድምፃዊ አስቻለው ፈጠነን ወደ ዝግጅታችን ስንጋብዘዉ፤ በደስታ ብሎ ወደ ቃለ-መጠይቅ ገባን፤ እንኳን ደስ ያለህ አልነዉም። እግዚአብሔር ያክብርልኝ፤ እኔንም ደዉላችሁ የጣብያችሁ እንግዳ ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ፤ ሲል ለቃለ-ምልልስ ዝግጁ ሆነ።      አርቲስት አደም መሐመድ - ሹቢቱ (ሽቶ)   

ከያኒ አስቻለዉ ብዙዎቹ ሙዚቃዎችህ እናትዋ ጎንደር ፤ አሞራዉ ከአሞራዉ እንገር ወሎ የተባሉት ሙዚቃዎችን ጨምሮ  ባህላዊም ናቸዉ፤ ዘመናዊም ናቸዉ፤ ብቻ በአድማጭ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝተዋል፤ እንዴት ተሳካልህ?

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነምስል፦ Aschalew Fetene

«እንግዲህ ሙዚቃ መቆፈርን ይጠይቃል። ብዙ ጥረትን ይጠይቃል። የራስ ፍልስፍናን እና መፈለግን ይጠይቃል። እኔም ብዙ ጥረት አደርጋለሁ። ጓደኛዬም ማለትም የሙዚቃዉ ዳሪክተር ሰዉመሆን ይስማዉ ብዙ ጥረት ያደርጋል ጎበዝ ነዉ። ተመካክረትን ተግባበን ስለምንሰራ ስኬታማ ሆነናል። የሙዚቃዉን ግጥሞች በአብዛኛዉ እኔ ነዉ የምጽፋቸዉ ጓደኛዬም የብዙዎችን ሙዚቃዎቼን ግጥምm ጽፏል። እኔ አሁን በይበልጥ ትኩረቴ ሙዚቃዉ ላይ እና ዜማዉ ላይ ነዉ።»

አስቻለዉ ፈጠነ ሙዚቃ «አሞራዉ ካሞራ» በተሰኘዉ የሙዚቃ ስራዉ ላይ የሚጠቀሱት አሞራዉ ዉብነህ ወይም ደጃዝማች ውብነህ ተሰማ ከ 1928 እስከ 1933 ዓ.ም ድረስ ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጽያን በወረረች ወቅት በዝያን ግዚዉ ምዕራብ በጌምድር ግዛት በተደረገ የፀረ ፋሽስት ትግል ግንባር ቀደም መሪ አርበኛ እንደነበሩ የታሪክ ማህደራት ያሳያሉ። አስቻለዉ ፈጠነ በዚህ ዜማዉ ላይ የሚሰሙት ግጥሞች ታሪካዊ ዳራ ያላቸው የአሞራው ውብነህ ተሰማን ታሪክ እና ፀባይ ቁልጭ አደርገዉ የሚገልጹ መሆናቸዉን ታሪካቸዉን የሚያዉቁ ይናገራሉ። ራስ አሞራው ውብነህ የፋሽስትን ጦር የሰማይ አሞራ ሆነው መቆሚያ መቀመጫ ያሳጡ ጀግና እንደነበሩ ይነገርላቸዋል። የዚህን ሙዚቃ ግጥም የደረሰዉ ከያኒ አስቻለዉ ፈጠነ እንደነገረን የሙዚቃዉ ግጥም ደራሲ ወንድሜ የሚለዉ ኃይለየሱስ ደርብ እንደሆን ተናግሯል።   

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነምስል፦ Aschalew Fetene

ከያኒ አስቻለዉ ፈጠነ «አሞራው ካሞራ» በተሰኘው ሙዚቃ ሥራው…ፊላ የደራሼ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ

ያየም ሰው ይናገር የነበረም ያውጋ፤

ተጋጥሟል ይባላል አሞራው ከአሞራ፤ 

ጎንደር ጀግና ትውለድ ታሳድግ ፀንሳ፤

እንደአሞራው ውብነህ ስሙ ማይረሳ … ሲል ጆሮ ሳይጎረብጥ በሚንቆረቆረዉ ድምፁ ጀግናውን ያስታዉሳል። ታሪኩን እያነሳም ያወድሳል። ልጃቸው ኢትዮጵያ ውብነህ በአገር ዉስጥ ቴሌቭዝን ላይ ቀርበዉ፤ ከነፃነት በኋላ እንግሊዞች ጎንደር ገብተው የራሳቸውን ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቅሉ የተመለከቱት ራስ አሞራው ውብነህ፤ በአገሬ ላይ የውጭ ሀገር ሰንደቅ ዓላማ አይሰቀልም በማለት እንግሊዞችን አስገድደው ባንዲራቸዉን አውርደው በምትኩ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንዲሰቀል እንዳደረጉ ተዘግቧል።አንጋፋው ድምጻዊ ጌታቸው ካሣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነምስል፦ Aschalew Fetene

ከሱዳን ገዳሪፍ ተስቦ እንደ ሰርዶ፤

ኢትዮጵያን ሰቀላት ያን ሰንደቅ አውርዶ፤

የአበቅየለሽ ልጆች ዳር እስከዳር ኩሩ፤

ጎንደር ጀግና አታጣም አትጠራጠሩ … በማለት አስቻለው “አሞራው ካሞራ” በተሰኘው ሙዚቃ ላይ የተቀኘለትም ለዚሁ ነው።

ራስ አሞራው ውብነህ በተወለዱ በ94 ዓመታቸው መስከረም 1975 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉን እና ሥርአተ ቀብራቸዉም አዲስ አበባ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል መፈፀሙ ታሪካቸዉ ያሳያል። ከያኒ አስቻለዉ ፈጠነ ቀደም ሲል ያወጣቸዉ ሙዚቃዎች፤ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ማግኘት የጀመሩት ሙዚቃዎቹ ከተለቀቁ በኋላ ቆየት ብሎ ነዉ። ልምን ይሆን።  አስቻለዉ ፈጠነ ሙዚቃን የጀመረዉስ መቼ ይሆን?

«ሙዚቃን የጀመርኩት በልጅነቴ ነዉ። ወላጆቼ እግር ስር ተቀመጬ እዘፍን ነበር። ክራር እጫወታለሁ ኪቦርድም እጫወታለሁ።» ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነ ታዋቂዉ ኢትዮጵያዊ የፊልም ስራ ባለሞያ ፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማ በመጭዉ መስከረም ወር ላይ በሚያስመርቁት እና ከ30 ዓመታት በላይ የሰሩት «BLACK LIONS, ROMAN WOLVES: THE CHILDREN OF ADWA» በተሰኘዉ ፊልም ላይ በሙዚቃ መሳተፍክን ሰምቻለሁ፤ እስቲ ስለሱ አጫዉተን።

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነምስል፦ Aschalew Fetene

«ፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማ እየሰሩት ባለዉ እና 30 ዓመታት በፈጀባቸዉ ፊልም ላይ እኔ ሙዚቃዎቼን ለማካተት እድል አጋጥሞኛል። በፊልሙ ዉስጥ የተካተቱት ሙዚቃዎች አዲስ እና እስከዛሬ ያልተሰሙ ናቸዉ። እኔ ፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማን በመተዋወቄ እጅግ እድለኛ ነኝ። እሳቸዉም ሙዚቃዬን አድምጠዉ በጣም ተደስተዋል። የምስጋና ደብዳቤ ሁሉ ጽፈዉልኛል። እና በጣም እድለኛ ነኝ። ምናልባት ፊልማቸዉ ሲመረቅ መስከረም ወር ላይ እኔም በምረቃዉ ሥነ-ስርአት ላይ እገኝ ይሆናል።»ዲንካ ባሕላዊ የዳዋሮዎች የሙዚቃ መሳሪያ

ፕሮፊሰር ኃይሌ ገሪማ ለፊልማቸዉ ይሆናል ያሉትን ሙዚቀኛ ከነቅላጼዉ በማግኘታቸዉ እጅግ እንደተደሰቱም አስቻለዉ ተናግሯል። አጋጣሚዉ በጣም የሚያስደንቅ aseደንቅ ነዉ ሲልም ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነ ይናገራል።   ከያኒ አስቻለዉ ፈጠነ እስካሁን በመድረክ ሙዚቃዉን ለህዝብ አቅርቦ አያዉቅም። ይሁን እና ከሳምንታት በኋላ ለፋሲካ በዓል አገረ እስራኤል ላይ የመጀመርያዉን የሙዚቃ ድግስ በመድረክ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አጫዉቶናል።

«እናትዋ ጎንደር» ተደማጭነትን ያገኘዉ ሙዚቀኛ አስቻለዉ ፈጠነምስል፦ Aschalew Fetene

 ጎጃም አገዉ ምድር ቻግኒ በሚባል ቦታ ተወለድኩ እዝያዉ ነዉ ያደኩት። እንዳጋጣሚ ሆኖ ቻግኒ ቀበሌ አንድ ልዩ ስፍራዉ መድሐንያለም በሚባል ቦታ ነዉ ተወልጂ ያደኩት፤ ታዋቂዋ ኢትዮጵያዊት አንቃኝ ጂጂ ሽባባዉም ከዚሁ ስፍራ እና አካባቢ ነዉ የወጣችዉ።  ሙዚቃ የጀመርኩት አባቴም ቤተሰቦቼም ክራር ይጫወቱ ስለነበር። እነሱ እግር ስር ቁጭ ብዬ እኔም ክራር መደርደርን ተማርኩ። ቦክስ ጊታር እሞክራለሁ። በግብርና በከፍተኛ የትምhreት ተቋም ዉስጥ ተመርቄ ስራ ስሰራ ነበር። ጥበብ ጠርታኝ  አዲስ አበባ መዘጋጃቤት ተቀጥሪ የሙዚቃ ስራዎቼን ሳቀርብ ነበር። እዝያዉ የሙዚቃ ችሎታዬን አዳብሪ እንግዲህ ዛሬ እዚህ ደርሻለሁ። በተለይ የምጫወተዉ ባህላዊ የሃገረሰብ ሙዚቃዎችን ነዉ በማህበረሰቡ ዘንድ ሙዚቃዎቼ ከፍተኛ ተቀባይነትን እያገኙ ነዉ።

ሙሉዉን ዝግጅት የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን! 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

 

Azeb Tadesse Hahn Azeb Tadesse
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW