«እንቡጥ» የኢትዮ - ፈረንሳይ መርጃ ማኅበር
ሰኞ፣ ኅዳር 8 2007ማስታወቂያ
በጎርጎረሳዉያኑ 1996 ዓ,ም ፈረንሳይ ዉስጥ ህጋዊ ሆኖ ተመስርቶ ችግረኛ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎችን ከፍተኛ እገዛ እየሰጠም ነዉ። ማኅበሩ በተለይ አዲስ አበባ ሾላ አካባቢ በሚገኘዉ «አድዋ በር» የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ዉስጥ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸዉ ቤተሰቦች የመጡ ተማሪዎችን፤ ወላጆቻቸዉን በሞት የተነጠቁ ችግረኛ ልጆችን እንዲሁም አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን እንደሚረዳ ታዉቋል። እነዚህ ተማሪዎች ከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን እስኪያጠናቅቁ ድረስ መማሪያ ቁሳቁስ በመስጠት ለተወሰኑ ተማሪዎች ደግሞ የኪስ ገንዘብ ሁሉ በመስጠት ድጋፍ ያደርጋል። የርዳታ ማኅበሩ ችግረኛ ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን የሚረዳዉ፣ በተጨማሪ ለትምርት ቤቱ የመማርያ ቁሳቁሶችን ይሰጣል።
ሐይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ