1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እንወያይ፤ በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለ ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ሰኔ 16 2016

በኢትዮጵያ ዉስጥ ግጭትና ጦርነት ሴቶች ይበልጥ ግፍ ደርሶባቸዋል፤ እየደረሰባቸዉም ነዉ። ጾታዊ ጥቃትና ማዋከቦችን ለመግታት ከመንግሥትም ሆነ ከሴቶች ማህበራት በቂ ድጋፍ አልታየም ይባላል። እንደሚታወቀዉ ሴት እናት፤ እህት፤ ሚስት፤ ልጅ ናት። ለኢትዮጵያዉያን ደግሞ አገርም ናት። ግን ሴቶች ላይ እየደረሰ ያለዉ ሰቆቃ ለምን ትኩረት አልተሰጠዉም?

ጾታዊ ጥቃት የደረሰባት ሴት
ጾታዊ ጥቃት የደረሰባት ሴት ምስል Nariman El-Mofty/AP/picture alliance

እንወያይ፤ አሳሳቢዉ በሴቶች ላይ የሚሰነዘር ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ

This browser does not support the audio element.

እንወያይ፤ አሳሳቢዉ በሴቶች ላይ ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በሚታየዉ ግጭት እና ጦርነት ሴቶች እና ህጻናት ይበልጥ ተጎጅዎች መሆናቸዉን የተለያዩየሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታዉቀዋል። ተቋማቱ ግጭት እና አለመረጋጋት በሚታይባቸዉ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በጾታዊ ጥቃት ሕይወታቸውን የሚያጡ፣ አካላቸው የሚጎድል ሴቶች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑንም ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት፡ በጉጂ እና ምዕራብ፤ ጉጂ ዞኖች ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች፤ ሴቶች እና ልጃገረዶች አሰቃቂ ጾታዊ ጥቃት፤ አስገድዶ መድፈር፣ ከባድ ድብደባ ደርሶባቸዋል፤  ለመዋረድ ተዳርገዋል፤ ይህም ስቃያቸውና ጉዳታቸውን እንዲባባስ አድርጓል፤ ሲል የመብቶች እና የዴሞክራሲ ማዕከል በእንግሊዝኛው ምህፃሩ /CARD/ካርድ ሰሞኑን ይፋ ባደረገዉ መግለጫ አስታዉቋል።

ግጭት እና ጦርነት በሚታይባቸዉ በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች  በሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈር፣ ድብደባ፣ ግድያና ሌሎች ፆታዊ ጥቃቶች መጨመራቸው፤ ቢታወቅም በሴቶች ላይ የሚደርሰዉን ይህንን  ጥቃት  ለመግታት እየተሰራ አይደለም የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። ከሁለት ዓመት ጦርነት እያገገመች ባለችዉ ትግራይ ክልልም የግጭት እናየአስገድዶ መደፈር ሰለባ የሆኑ ሴቶች ዛሬም ድረስ ከሥነ-ልቡና እና ከአካላዊ ጉዳት አላገገሙም።

በዚህ ሳምንት  ረቡዕ በግጭት እና ጦርነት አካባቢዎች የሚፈፀሙ የፆታ ጥቃቶችን ለማስቀረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንዛቤ የሚሰጥበት ዓመታዊ ቀን ታስቦ ዉሏል። በዓለም ዙሪያ በውሳኔ ሰጭ መድረኮች ላይ የሴቶች ቁጥር በመቀነሱ ግጭቶችን በመፍታት ወይም የጤናና የኑሮ ደረጃን በማሻሻል ረገድ እድገት እንዳይኖር እንቅፋት መሆኑ በተመድ ባለስልጣናት ተገልጿል። በኢትዮጵያስ?

በግጭት እና ጦርነቶች ዉስጥ ይበልጥ ተጎጅ ለሆኑት ሴቶች መፍትሄ  ያልተገኘዉ ለምድንድን ነዉ? ግጭት ጦርነት ብሎም በመላዉ ሃገሪቱ የሴቶች የሰብዓዊ መብት ይዞታ ምን ይመስላል?

በሴቶች ላይ የሚደርሰዉን ጾታዊ ጥቃት እና ማፈናቀል ብሎም የተለያዩ ጥቃቶች እና ማዋከቦችን ለመግታት ከመንግሥትም ሆነ ከሴቶች ማህበራት ድጋፍ አልታየም ይባላል። እንደሚታወቀዉ ሴት እናት ናት፤ እህት ናት፤ ሚስት ናት ፤ ልጅ ናት፤ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን ደግሞ አገርም ናት። ኢትዮጵያ እናታችን ብለን በእናት ነዉ የምንሰይማት።  እና  የሴቶች ችግር ግን ትኩረት አልተሰጠዉም። የሴቶች ተቋማት እንደሌሎች ሰብዓዊ ተቋማት ድምጻቸዉን ከe አድርገዉ ለምን ማሳማት አቃታቸዉ ምን እየሰሩ ነዉ? ሲሉ ብዙዎች ይጠይቃሉ። እንወያይ የሚያነሳዉ ጉዳይ ነዉ።  

በዉይይቱ የተሳተፉት፤

1, መሰረት ዓሊ ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች ለኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር

2, ብርሃን ገብረክርስቶስ፤   በተለይ ጥቃት የደረሰባቸዉን ሴቶች በማገዝ የሚታወቁ

3,   ወይዘሮ ትጥቅነሽዓለሙ   የሴት ሰብዓዊ ተሟጋች  እንዲሁም

4, መሱድ ገበየሁ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥምረት ዋና ዳይሬክተር

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW