1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እንወያይ፤ የበቀል ፖርኖግራፊ - የበይነ መረብ ሰላባ የሆኑት ወጣት ኢትዮጵያዉያን

Azeb Tadesse Hahn
እሑድ፣ ጥር 11 2017

የወጣት ኢትዮጵያዉያት የእርቃን ፎቶና ቪዲዮዎች በኢንተርኔት የበቀል መሳርያ እየሆኑ መምጣታቸዉ እያነጋገረ ነዉ። ያለፈቃድ የሚለቀቁት እነዚህ ምስሎች የገንዘብ ማግኛ ምንጭ መሆናቸዉ ደግሞ ነገሩን አሳሳቢ አድርጎታል። በኢንተርኔቱ ጨለማ ዓለም ታስረዉ እራሳቸዉን እስከማጥፍት የሚደርሱ ጥቂቶች አይደሉም። መፍትሄዉ ምንድን ነዉ? ሃሳባችሁን አካፍሉን!

የበቀል ፖርኖግራፊ - የበይነ መረብ ሰላባ የሆኑት ወጣት ኢትዮጵያዉያት
የበቀል ፖርኖግራፊ - የበይነ መረብ ሰላባ የሆኑት ወጣት ኢትዮጵያዉያት ምስል Nebiyu Geberemichael - Shega

የበቀል ፖርኖግራፊ - የበይነ መረብ ሰላባ የሆኑት ወጣት ኢትዮጵያዉያት

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች የእርቃን ፎቶና ቪዲዮዎች በኢንተርኔት(በበይነ መረብ) የበቀል መሳርያ እየሆኑ መምጣታቸዉ እያነጋገረ ነዉ። በተለይም ወጣት ሴቶች እርቃናቸውን የሚታዩባቸዉ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በቀድሞ ፍቅረኞቻቸዉ ያለፈቃዳቸዉ በበይነ መረብ የሚለቋቸው ቪድዮዎችን ፎቶዎች የገንዘብ ማግኛ ምንጭ መሆናቸዉ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል። በቅርቡ ይፋ የሆነ አንድ የምርመራ ዘገባ እንደሚያመለክተዉ፤ በርካታ ሴቶች በተመሳሳይ ጥቃት፤ ተሰብረዉ፤ በኢንተርኔቱ ጨለማ ዓለም ዉስጥ ታስረዉ፤ ከዚያም አልፎ በደረሰባቸዉ ስብራት እራሳቸዉን ለማጥፋት የሚወስኑ ሴቶች ጥቂቶች አይደሉም።

የሴቶችን እርቃን የሚያሳዩ ወይም ወሲባዊ ስሜትን የሚቀሰቅሱ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች ፣ያለ ባለቤቱ  ፈቃድ፤ ለበቀል በኢንተርኔት እየተለቀቁ፤ ፖርኖግራፊ ወይም የወሲብ ድርጊቶች የሚሰራጩበት ድረ-ገፆች እና በተለይም ቴሌግራም ቻናሎች ቋሚ ገንዘብ ማግኛ እየሆኑ ነው። ድርጊቱ እየተስፋፋ ወጣት ሴቶች እየተበዘበዙ፤ ከማኅበረሰቡ እንዲገለሉ እየተደረገ መሆኑን፤ በዚህ ላያ ያተኮረው የምርመራ ዘገባ ያመለክታል። ከዚህ ሌላ ወደ አረብ አገር፤ ለስራ ኮንትራት ተብሎ ከሚሄዱ ወጣት ሴቶች መካከል ለተመሳሳይ ችግር የወሲብ ብዝበዛ መዳረጋቸው እየተነገረ ነዉ።

በኢትዮጵያ ወይም በአበሻ ስም የወሲብ ድርጊቶች የሚቸበቸብባቸዉ ድረ-ገፆች  አሳሳቢነት በይፋ አይነገር እንጂ፤ ጉዳዩ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ይህ ወንጀል፤ ቁጥጥር ካልተደረገበት በኢትዮጵያ  ቁጥራቸው ከፍተኛ እንደሆነ የሚገመት ወጣት ሴቶች ሕይወት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ እና የማህበራዊ ቀውስም እንደሚያስከትል ስጋት አለ። ብዙም የማይወራለት ግን አሳሳቢ የሆነው የበቀል ፖርኖግራፊ -ሰለባ የሚሆኑ  ወጣት ሴቶች ጉዳይ እንዴት ነው መፍትሄ ሊያገኝ የሚችለዉ? በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወያዩ አራት እንግዶች ጋብዘናል እነርሱም፤

የበቀል ፖርኖግራፊ - የበይነ መረብ ሰላባ የሆኑት ወጣት ኢትዮጵያዉያት - ቴሌግራምምስል Nebiyu Geberemichael - Shega

1,ወ/ሮ መሰረት አዝግ  መሰረት በኢትዮጵያ የሴቶች እና የህጻናት በጎ አድራጎት ድርጅት ዳይሬክተር  

2  ብርሃን ገብረክርስቶስ በትግራይ ነበበረዉ ጦርነት የፆታ ጥቃት እና አስገድዶ መድፈር የደረሰባቸዉን ሴቶች በማገዝ የሚሰሩ፤ በሴቶች ጉዳይ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን የሚያደርጉ፤  

3, ጋዜጠኛ ቃልአብ ግርማ  -በመይነ መረብ፣ የበቀል ፖርኖግራፊ ወይም የወሲብ ድርጊቶች የሚሰራጩበት ድረ-ገፆች እና በተለይም ቴሌግራም ቻናሎች በኢትዮጵያ ቋሚ ገንዘብ ማግኛ መሆናቸዉን ለስድስት ወራት ምርመራ አድርገዉ ዘገባ የጻፉ፤  እንዲሁም

4, ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በተለያዩ አረብ ሃገራት የኖሩ እና በኢትዮጵያዉያን ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ሥራዎችን የሰሩ እና ዘገባዎችን የጻፉ፤ ናቸዉ።  

-በበይነመረብ ፤ በቴሌግራም ቻናል የታዳጊ ሴቶችንና ሴቶች ፎቶ ቪዲዮ በኢንተርኔቱ ዓለም ያለፈቃድ መልቀቅ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መልቀቅ ብሎም ለፖርኖግራፊ ሽያጭ ወይም የፆታ ስሜትን መቀስቀሻነት ማዋል ፤ ድብቅ ወንጀል ነዉ ። በተለይ በኢትዮጵያ የተለመደ አይደለም። እንደዉ ጥልቀቱ ምን ያህል ነዉ? የስብራቱ መጠን ?

-በቀድሞ ፍቅረኛ እጅ በማኅበራዊ መገናኛ ቴሌግራም የሚለቀቀዉ ይህ የሴቶች የራቁት ፎቶ እና ቪዲዮ የሚያስከትለዉ ማኅበራዊ ቀዉስ፤ እና በሰዎች ላይ ሊያደርስ የሚችለዉ ጉዳት እንዴት ነዉ የሚታየዉ?

-መንግሥት በበበይነ መረብ ያለፈቃድ የሚለቀቁ ቪዲዮችን መቆጣጠሪያ  ህግ አለው ? 

የበቀል ፖርኖግራፊ - የበይነ መረብ ሰላባ የሆኑት ወጣት ኢትዮጵያዉያት ምስል Nebiyu Geberemichael - Shega

-በአጠቃላይ እንዲህ አይነቱን ወንጀል መከላከል ለፍርድ ማቅረብ የሚቻልባቸዉ ዘዴዎች ምንድን ናቸዉ? አዳዲስ ህጎች ያስፈልጋሉ? እንዴት ነዉ መብትን ማስከበር የሚቻለዉ? ያለፈቃድ ያለ እዉቅና እንዲህ አይነት ነገር ሲፈፀም የሚከታተል፤ ካሳም የሚያሰጥ ወንጀለኛዉንም የሚያስቀጣ ህግ ኢትዮጵያ ዉስጥ አለ?

-ማኅበረሰቡ ልጆቹን ለማዳን ከመንግሥት ጋር በምን አይነት ቁርኝት መስራት ይችላል? ወንጀለኞችስ በቃችሁ ሊባሉ አይገባም ወይ?  

-ይህ አይነቱ ወንጀል በቴክኖሎጂ የታገዘ ነዉ፤  ከእንዲህ አይነቱ ወንጀል እንዴት ነዉ መጠንቀቅ የሚቻለዉ? መከላከልስ የሚቻለዉ? ጉዳዩ በይፋ ውይይት እንዲካሄድበት  ምን ሊደረግ ይገባል?

ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማስመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እናጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ     

Azeb Tadesse Hahn Azeb Tadesse
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW