1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ.ም እንወያይ፤ «የጦርነት ዳመና»

እሑድ፣ መስከረም 11 2018

ህወሐት በአለፈው እሁድ ባሰራጨው መግለጫ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስትን የፕሪቶርያ ውል በመጣስ በትግራይ ግጭት ለመፍጠር በአፋር እና በምዕራብ ትግራይ ታጣቂዎች እየመለመለ እና እያስታጠቀ ነው ሲል ከሷል።

የተለያዩ የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚሰጡአቸው መግለጫዎችም ለጦርነት ዝግጁና ብቁ መሆናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
የተለያዩ የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚሰጡአቸው መግለጫዎችም ለጦርነት ዝግጁና ብቁ መሆናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።ምስል፦ Fotolia/chris-m

እንወያይ፤«የጦርነት ዳመና»

This browser does not support the audio element.

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መስተዳድር ፕረዚደንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በቅርቡ  በመቐለ ከተማ በተካሄደው የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላይ  በሰጡት አስተያየት በትግራይ ክልል የጦርነት ዳመና እያዳመነ እንደሆነ ገልጸዋል።

"ብሔራዊ አንድነት ለህልውናና ደህንነትን ለማረጋገጥ" በሚል መሪ ሐሳብ ለሁለት ቀናት በተካሄደ የህወሐት ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ  ሲጠናቀቅ ተሳታፊዎች ባወጡት የአቋም መግለጫም  «የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ በኩል ለሚቀርቡ ሕገመንግስታዊ ጥያቄዎች ምላሹ ማስፈራራት ሆንዋል» ሲሉ ከሷል።

ከዚህ በተጨማሪ የፌደራል መንግስት በትግራይ የእርስበርስ ግጭት ለመፍጠር ታጣቂዎች እያደራጀ ነው ሲል ህወሓት ከሷል። ይህ አካሄድ «የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የሚያፈርስ ነው» ብሏል። 

ህወሐት በአለፈው እሁድ ባሰራጨው መግለጫ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስትን የፕሪቶርያ ውል በመጣስ  በትግራይ ግጭት ለመፍጠር በአፋር እና በምዕራብ ትግራይ ታጣቂዎች እየመለመለ እና እያስታጠቀ ነው ሲል ከሷል።

በፌደራል መንግስት በኩል ደግሞ ሕወሐት ከኤትራ መንግስት ጋር እያካሄደ ነው ያለውን ግኑኝነት ኢሕገመንግስታዊ መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት ወደ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል በተደጋጋሚ አስጠንቅቋል። የትግራይ ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራም በፌደራል መንግስት በኩል ዝግጁነትና ፍላጎት ቢኖርም  በህወሐት በኩል ዕንቅፋት እየገጠመው እንደሆነ ይገልጻል።

የተለያዩ የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ መሪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚሰጡአቸው መግለጫዎችም ለጦርነት ዝግጁና ብቁ መሆናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ። በትግራይ ክክል ዳግም  የጦርነት ዳመና እያንዣበበ ይሁን? መፍትሔው ምንድነው? የዛሬ ውይይታችን ርዕስ ነው። ማድመጫውን በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ያዳምጡ።

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW