1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

እንወያይ፤ ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት በአማራ ክልል

እሑድ፣ ኅዳር 28 2018

ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በኢትዮጵያ ስር የሰደደ ችግር ቢሆንም፣ በአገሪቱ እየተከሰቱ ባሉ የትጥቅ ግጭቶች ሳቢያ ጥቃቱ እየተባባሰ መምጣቱ ይነገራል። በአማራ ክልል ላለፉት ሁለት አመታት በፌደራል መንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭትም በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ወሲባዊ ጥቃት ማባባሱን የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት
በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ግጭቶች በሴቶች ላይ የሚፈፀ።ሙ ወሲባዊ ጥቃቶች እንዲባባሱ አድርጓል።ምስል፦ Nariman El-Mofty/AP/picture allianc

እንወያይ፤ ጦርነት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት በአማራ ክልል

This browser does not support the audio element.

 

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጎርጎሪያኑ ህዳር 25 እስከ ታህሳስ 10  እየተካሄደ ያለውን «የፆታን መሰረት ያደረገ  ጥቃት ይቁም  የ16 ቀናት ዘመቻ » ምክንያት በማድረግ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት  ከሶስት ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ ጾታዊ ጥቃት ይደርስባታል።ጥቃቱ በአብዛኛው የቅርብ በምትለው ሰው የሚፈፀም ነው።

ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በኢትዮጵያ ስር የሰደደ ችግር  ሲሆን፣ በአገሪቱ እየተከሰቱ ባሉ የትጥቅ ግጭቶች ሳቢያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ። 
ቀደም ሲልም በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ለሁለት አመታት የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ተከትሎ  በትግራይ ክልል  በሴቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጾታዊ ጥቃት ተፈፅሟል።ቁጥሩ ይለያይ እንጅ  ጦርነቱ በተስፋፋባቸው የአማራ እና አፋር ክልሎችም ጥቃቱ መፈፀሙን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ገልፀዋል።

በአማራ ክልልምላለፉት ሁለት አመታት በፌደራል መንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭትም ይህንኑ ጾታዊ ጥቃት ማባባሱ ይነገራል።የአማራ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሰሞኑን አዲስ ማለዳ ለተባለ አንድ የሀገር ውስጥ መገናኛ ዘዴ እንደገለፀው በመንግስትና በፋኖ ሃይሎች መካከል በተፈጠረው እና ከሁለት አመታት በላይ በዘለቀው ግጭት ህጻናትን ጨምሮ 3,036 ጾታዊ ጥቃቶች ተመዝግበዋል። በክልሉ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ  ቢቢሲ በቅርቡ ባወጣው የምርመራ ዘገባም ከ2600 የሚበልጡ ሴቶች በመንግስት ወታደሮች መደፈራቸውን አመልክቷል።
የሕግ አስከባሪ አካላት መዋቅር መፈራረስ፣ የታጠቁ አካላት መብዛት፣ መፈናቀል እና የጤና ጥበቃ አገልግሎቶች መስተጓጎል  ሴቶችን ለወሲባዊ ጥቃቶችእንዲሁም  ጥቃቱን ተከትሎ ለሚመጣ ጉዳት እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል።እነዚህ ጥቃቶች በጥቃቱ ሰለባዎች ላይ ከባድ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት ከማድረስ ባለፈ ቤተሰቦችን ያፈራርሳሉ፣ ማህበረሰብን ያናጋሉ ፣ ዘላቂ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መዘዞችም ያስከትላሉ።
ግጭት ያባባሰው ወሲባዊ ጥቃት በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል የዛሬው የእንወያይ ዝግጅት ትኩረት ነው።

ይህ ውይይት በሴቶች ወሲባዊ ጥቃቱ አባባሽ ምክንያቶች፣በጥቃቱ ሰለባዎች እና በማህበረሰቡ ላይ ሀገር የሚያደርሰው ጉዳት ምንስ መደረግ አለበት የሚለውን ይዳስሳል።

 

በውይይቱ የተሳተፉ፤
⦁ ዶክተር ስህን ተፈራ፤ ሴታዊት የተባለ በጾታ ፍትህ ላይ የሚሰራ ተቋም መስራች እና  ዳይሬክተር
⦁ ማህሌት ዳዲ ገብረመስቀል፤ የአፍሪቃ የሴቶች ሰላም እና ፀጥታ ተቋም የፕሮግራም ማኔጀር  
⦁ አቶ ያሬድ ሀይለማርያም ፤የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና የቀድሞው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ናቸው።

ሙሉ ውይይቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።

ፀሐይ ጫኔ

 

 

 

 

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW