እንደገና የሚቀናበሩ ሙዚቃዎች በኢንደስትሪው ውስጥ ያላቸው አንድምታ
እሑድ፣ ሚያዝያ 2 2014
ሙዚቃ በኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ሂደት እያለፈ ዛሬን ደርሷል። በየትውልዱ ዘመን ተሻጋሪ የሙዚቃ ስራዎች ተሰርተው ለአድማጭ ተመልካቹ ደርሰዋል። የዚያኑ ያህል ከግለሰቦች ድካም ሳይዘል በአንድ ወቅት ተደምጠው በሆነ አጋጣሚ ካልሆነ በቀር ከአድማጭ ተመልካቹ ጆሮና አይን ርቀው የቀሩ የሙዚቃ ስራዎች ተጠቃሾች ናቸው ። ባለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ደግሞ ሙዚቃ ፣ የሙዚቃ ስራ እና ሙዚቀኛ በሌላ የታሪክ ምዕራፍ ሊዳኙ ስራዎቻቸውን በገፍ እያቀ,ረቡልን ነው ። ጤና ይስጥልን የዝግጅታችን ተከታታዮች በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደገና በሚሰሩ ወይም በእንግሊዘኛው ሪሚክስ በሚደረጉ እንዲሁም በከቨር የተሰሩ አዳዲስ የነጠላ ዜማዎች በስፋት እየተለቀቁ መሆናቸውን ተከትሎ በሀገሪቱ የሙዚቃ ዕድገት ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና በተመለከተ የመጀመሪያውን ክፍል ማስደመጣችን ይታወሳል።
በዛሬው የሁለተኛ ክፍል ዝግጅታችን ቀጥለን አንጋፋ የሙዚቃ ሙያተኞችን ሃሳብ አካተን የሙዚቃችን መንገድ ወዴት ስንል መጠየቃችንን እንቀጥላለን አብራችሁን ቆዩ።
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በሙሉ የሙዚቃ ኦርኬስትራ የታጀበ የሙዚቃ ስራ ለአድማጭ ተመልካች በመቅረብ የ194oዎቹ መገባደጃ አመታት አዲስ ታሪክ የጸፉበት ዘመን ነበር። በወቅቱ በተናጥል በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች አልያም ባልተሟሉ የሙዚቃ መሳሪያዎች ታግዘው ይሰሩ ለነበሩ ድምጻዊያን ለአዲስ የታሪክ ምዕራፍ በር እንደከፈተላቸው ይነገራል። ለዚህ ደግሞ በዋናነት አንጋፋው የሙዚቃ ሰው አመሃ እሸቴ ከሱዳን እና ከሌሎች የምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት የሚያመጣቸውን የሙዚቃ ስራዎች በድምጽ ማጉያ ታግዞ ለአድማጮች ማድረሱ እና ለተመሳሳይ ስራ ድምጻዊያንን መጋበዙ ዛሬ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ስማቸውን በደማቁ አስጽፈው ላለፉት ድምጻዊያን መገለጥ መሰረት ጥሏል። ዛሬ ባለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን በእንደገና ወይም በእንግሊዘኛው ሪሚክስ የሙዚቃ ስራዎች ላይ ለሚነሱት የተለያዩ አስተያየቶች መነሻቸውም ከዚሁ ነው። አንጋፋው ድምጻዊ ጸሐዬ ዮሐንስ ቀደምት የሙዚቃ ስራዎችን በሪሚክስ መስራትን «ውድቀት » ሲል ይገልጸዋል። የሰውን የሙዚቃ ስራ መልሶ መስራት ለሀገሪቱ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውድቀት ማሳያ ስለመሆኑ ቀዳሚው ትውልድ ያለፈበትን መንገድ በማስታወስ እንዲህ ይገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ጃዝ የሙዚቃ ፈጣሪው እና አንጋፋው የሙዚቃ ሰው ዶክተ,ር ሙላቱ አስታጥቄ እንደሚለው ፤ ከሞያዎች ሁሉ ፈጠራ ልቆ ሊታይበት የሚገባው የሙዚቃው እንደስትሪ እንደሆነ ያምናል ። ነገር ግን የትኛዉንም አይነት የሙዚቃ ስራ ከመፈረጅ በፊት የሙዚቃ ስራው ተሰርቶ ከአድማች ተመልካች ዘንድ ከቀረበ በኋላ ሊያሟላቸው የሚገባቸውን የሙዚቃ ግብአቶች አሟልቷል ወይ ብሎ መጠየቁ ተገቢ እንደሆነ ይገልጻል።
ወጣቱ የሙዚቃ አ,ቀናባሪ ነቢዩ ጥሩነህ ወይም ዲጄNX በርካታ የሪሚክስ ስራዎችን ከሰሩ የሙዚቃ አቀናባሪዎች ተጠቃሽ ነው። ነገ,ር ግን ለነቢዩ ያለፉት ስድስት ሰባት ዓመታት በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ፈጠራ እና ክህሎት ያልታዩበት ፤ በቪዲዮ ታግዘው የሚሰሩትም ቢሆኑ ገንዘብ እና ስም ማግኘትን መርህ አድርገው ሞያው ላይ ብርቱ ጉዳት ስለማድረሳቸው ምስክርነቱን ይሰጣል።
አዳዲስ ድምጻዊያን የቀደሙ ስራዎችን በአዲስ መልክ መስራት በሙዚቃው ዕድገት ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት በላይ ትውልዱ እየተጓዘ ያለበት የስነልቦና መንገድ ሌላ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ስጋቱን የሚገልጸው ጸሐዬ ዮሐንስ ፤ አ,ዲሱ ትውልድ ልክ እነርሱ በዘመናቸው በራሳቸው መንገድ ስም እንደተከሉ ሁሉ ጥሩ የተፈጥሮ ችሎታ ያለቸው ድምጻዊያን በራሳቸው ስራ ስማቸውን ቢተክሉ የተሻለ ነገን ይፈጥራሉ ሲል ይመክራል።
ወጣቷ ድምጻዊት ዘቢባ ግርማም ምንም እንኳ የቀደሙ ስራዎችን መስራት እስስካልተበላሸ ድረስ በራሱ ችግር እንደሌለው ብታምንም ከጥቅም ባሻገር በድካም ውስጥ ስለሚመጣ ታላቅነት እያሰቡ በትጋት መስራት የተሻለ ጊዜን ለማለም ያግዛል ባይ ናት ። ብዙዎች የሚሸሹት አድካሚ ነገር ግን አንጋፋዎቹ ያለፉበት መንገድ ።
በእርግጥ ነው የሙዚቃ ስራ እንደ አድማጩ እና ተመልካቹ ነው ። ለአንዱ ተደናቂ ለሌላው ላይሰራ ይችላል። በአንድ በኩል ደግሞ አብዛኛውን የሚያስማማ እና አድናቆት ሊቸረው የሚገባም በዚያው ልክ አይጠፋም። የሆነ ሆኖ ሙዚቃው እንደ,ጊዜው ሊዘምን እና በጊዜው ተዋጅቶ ሊያድግ ግድ ይለዋል። ያደግሞ ሂደቱን ጠብቆ ሞያዉን አስከብሮ እና ተከብሮ ማለፍን ይጠይቃል። በዚህ ረገድ የሙዚቃ ትምህርት ቤቶች የድምጻዊያን ማዳደሪያ መድረኮች የተሻለ አቅም ያላቸውን ድምጻዊያንን በማፍራት ሂደት ኃላፊነት አለባቸው። በየትውልድ ዘመኑ ስማቸውን እየተከሉ ያለፉቱ ለአዳዲሶቹ ቅርሳቸውን የማውረሳቸውን ያህል የሚገባቸውን ክብር ማግኘት ይኖርባቸዋል። እንግዲህ አድማጮቻችን ዝግጅታችን በዚሁ እንቋጭ ፤ የመዝናና ዝግጅታችን ሳምንት በሌላ ርዕሰ ጉዳይ ይጠብቃችኋል።
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ