ኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልል ወሰንን ተቃወመ
ዓርብ፣ ጥቅምት 4 2015
ኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ባወጣው መግለጫ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ አስተዳደሮች ያፀደቁትን የአስተዳደር ወሰን በኦሮሞ ህዝብ ላይ ታሪካዊ በደል ፈፅሚ ነዉ ብሎታል።
ለዘመናት ሲነሳ የቆየ ያለውን የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን አይመልስም ያለው መግለጫ፣ ውሳኔ የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄ የሚመልስ ሳይሆን መደናገርን ለመፍጠር እና ለዓመታት ሲካሄድ የነበረውን የከተማዋን ህገወጥ መስፋፋት እውቅና በመስጠት የህጋዊነት ካባ ለማልበስ ያለመ ነው ብሏል። ኦፌኮ የራሱን የባለሙያዎች መድቦ ድንበሩን እንዳስጠና፣ ሰነድና ማስረጃዎችን ማሰባሰብም በመግለጫው ገልፆል።
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ዋና ፀሀፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ፓርቲያቸዉ ጥናቱን ያደረገዉ የአዲስ አበባ መስተዳድርና የኦሮሚያ ክልል የደረሱበት ውሳኔ ብዙ ያልመለሰው ጥያቄ ስላለ ነው ብለዋል። «ፊንፊኔ ማን ናት በሀብትነት በይዞታ ነት የማን ህዝብ ናት የሚለውን ያልመለሰ ነው» ሲሉ «በልማት ተብሎም ይሁን በኬሚካል ለተፈናቀሉ ሰዎች ልጆች ለማኝ ለሆኑበት አባቶች ዘበኛ ለሆኑበት እናቶችም አፈናቃዩች ገረድ የሆኑበን ሁኔታ ምንም ያላነሳ መሆኑን ነው ጥናታችን ትኩረት አድርጎ የሰራው እነዚ መታረም እንዳለባቸው ድንበር እናካልላለን ያሉት መጀመሪያ ትኩተት ተሰቶት ያልተጠቀ እና ቢጠየቅ እንኩዋን 3ተኛ እና 4ተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን ግልፅ ለማድረግ ነው ጥናታችን ግልፅ ያደረገው» ብለዋል
ኦፌኮ በመግለጫው አዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ ወደ ኦሮሚያ የተስፋፋችው 11,000 (አስራ አንድ ሺህ) ሄክታር ብቻ ነው በማለት አሁን ከተማዋ ካለችበት ከ54,000 (ሃምሳ አራት ሺህ) ሄክታር ላይ በመቀነስ 43,000 ( አርባ ሶስት ሺህ) ሄክታር ስፋት እንዳላት እውቅና በመስጠት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ታሪካዊ በደል ፈፅመዋል ብልዋል።የአዲስ አበባ አዲስ ወሰን
የፊንፊኔ ከተማ አስተዳደር ላለፉት 28 አመታት የኦሮሞ ህዝብ ከከተማዋ ሊያገኝ የሚገባወን ጥቅም በመከልከሉ ኢ-ህገመንግስተዊ ተግባር ስለሆነ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች በአፋጣኝ ተጠንቶ ለደረሰው ጉዳት ካሳ ከነወለዱ ለኦሮሞ ህዝብ እንዲከፍል እንጠይቃለን ሲል ባወጣው መግለጫ አካትዋል። የአዲስ አበባ መስተዳድር እና ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የአስተዳደር ወሰንን ማካለል ውሳኔ ከተሰጠ ለሁለት ወራት ዘግያታችሁ ትላንት ውሳኔውን እንደምትቃወሙ ገልፃችኋል ለምን ዘገያችሁ ስል ለአቶጥሩነህላቀረብኩላቸው ጥያቄ «እኛ ፊንፊኔን በተመለከተ መግለጫ ስናወጣ የመጀመሪያችን አይደለም» ብለዋል ከ2006 ጀምሮ በየግዜው በመቃወም መግለጫ እናወጣለን ብለዋል «የኛ መቃወም አዲስ ነገር አይደለም የተወነውን የፖለቲካ ውሳኔ በመቃወም ነው እንጂ ምንም የዘገየ ነገር የለም። በጥናት ላይ በተደገፈሁኔታ ለማረብ ነው ይሄን ያህል ልንቆይ የቻልነው ተቃውሞአችንን ስንገልፅ ምክንያታዊ በሆነ ሁኔታ ለመግለጽ ነው» ብለዋል
የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የአስተዳደር ወሰንን ማካለልን ከዚ ቀደም የተለያዩ ፓርቲዎች ውሳኔውን እደማይቀበሉ መግለጫ አውጥተዋል ከነዚህም መሀከል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከወራት በፊት ባወጣው መግለጫ "አዲስ አበባን የመሰልቀጥ እና የነዋሪዎቿን መብት በጠራራ ፀሐይ የመግፈፍ ሥራ እየተከናወነ ነው" በማለት የአስተዳደር ወሰኑን መቃወሙን ገልጽዋል ።
እንዲሁም የኦሮሞ ነጻነተር ግንባር (ኦነግ)“በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር” እና በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን መካከል የነበረዉን የድንበር ውዝግብ ፈተናል በሚል በሁለቱ አስተዳደሮች የተሰጠውን መግለጫ ለሚድያ ፍጆታ ብቻ የወጣ ነው ሲል የወሰን ውሳኔው የህዝብ ውይይት ያልታከለበትና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ያልታከለበት በመሆኑ ለዘመናት ሲነሳ የቆየውን የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን አይመልስም ሲሉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በበኩሉ "ሕዝብ የአስተዳደር ውሳኔን የመቀበል ግዴታ የሚኖርበት እንደ ዜጋ ሂደቱ ላይ የመሳተፍ እና የማወቅ መብቱ በአግባቡ ሲከበርለት ብቻ ነው" ማለቱ ይታወሳል።
ማሕሌት ፋሲል
ነጋሽ መሐመድ