"ከህወሓት ጋር ተደራደሩ ማለት ስህተት ነው" ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ
ሰኞ፣ መስከረም 10 2014![Karte Sodo Ethiopia ENG](https://static.dw.com/image/43828395_800.webp)
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥትን ጨምሮ በትግራይ ውጊያ በሚሳተፉ ኃይሎች ላይ አሜሪካ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችል መመሪያ ማጽደቋን "ታሪካዊ ስህተት" ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ተቹ።
አሜሪካ የኢትዮጵያን ቀውስ ለመፍታት በምታደርገው ጥረት "ትክክለኛ አቅጣጫ እየተከተለች ነው ብለን አናምንም" ያሉት ዶክተር ቢቂላ ህወሓት እና የኢትዮጵያ መንግሥትን ዕኩል ማየት ተገቢ አይደለም ብለዋል። "አሸባሪነት፣ አክራሪነት እና ጥፋተኝነት እንዲወገድ የሚያደርግ እገዛ ማድረግ እንጂ እጅን አስረዝሞ ባልተገባ ሁኔታ ጣልቃ ለመግባት መሞከር ተገቢ አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።
ስዩም ጌቱ
እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ