1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከምስራቅ ወለጋ ሸሽተው አዲስ አበባ የተጠለሉ ተፈናቃዮች

ረቡዕ፣ ጥር 18 2014

ከምስራቅ ወለጋ የሸሹ 107 ነዋሪዎች አዲስ አበባ እስጢፋኖስ ቤተ-ክርስቲያን ተጠልለዋል። ከተፈናቃዮቹ 30 ሕፃናት ናቸዉ። የኢትዮጵያ መንግስት ኦነግ ሸኔ በሚል ስያሜ በአሸባሪነት የፈረጀዉ ሸማቂ ቡድን ታጣቂዎች ምዕራብ ኦሮሚያ ዉስጥ በተለያየ ጊዜ በሰላማዊ ሰዎች ላይ አደጋ እንደሚጥል በየጊዜዉ መዘገባችን አይዘነጋም።

Äthiopien | 200 Zivilisten finden Zuflucht in der orthodoxen Kirche in Addis Abeba
ምስል Solomon Muchie/DW

ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ለባለሥልጣናት ያቀረቡት አቤቱታ ሰሚ አላገኘም

This browser does not support the audio element.

እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ጦር ብሎ የሚጠራዉ ሸማቂ ቡድን ጥቃት ያደርስብናል ብለዉ ከምስራቅ ወለጋ የሸሹ 107 ነዋሪዎች አዲስ አበባ እስጢፋኖስ ቤተ-ክርስቲያን ተጠልለዋል። ከተፈናቃዮቹ 30 ሕፃናት ናቸዉ። የኢትዮጵያ መንግስት ኦነግ ሸኔ በሚል ስያሜ በአሸባሪነት የፈረጀዉ ሸማቂ ቡድን ታጣቂዎች ምዕራብ ኦሮሚያ ዉስጥ በተለያየ ጊዜ በሰላማዊ ሰዎች ላይ አደጋ እንደሚጥል በየጊዜዉ መዘገባችን አይዘነጋም። አዲስ አበባ የሰፈሩት ተፈናቃዮች እንደሚሉት በሕይወታቸዉና ንብረታቸዉ ላይ ያንዠበበዉን አደጋ መንግስት  እንዲከላከልላቸዉ ለወረዳና ለዞን ባለስልጣናት አቤት ቢሉም ሰሚ አላገኙም። አዲስ አበባ ከገቡት ተፈናቃዮች የተወሰኑት የቤተሰቦቻቸዉ አባላት ያሉበትን ሥፍራና ሁኔታ እንደማያዉቁ ዐስታዉቀዋል። 

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW