1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከምዕራብ ወለጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ ስለመታቀዱ

ቅዳሜ፣ ጥር 18 2016

ከምዕራብ ወለጋ ዞን ሶስት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸው ለመመለስ የወደሙ ቤቶችን መልሶ መገንባቱን የዞኑ ቡሳ ጎኖፋ/የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ ከጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ ዜጎችን በመጀመሪያ ዙር ለመመለስ 60 ያህል የወደሙ ቤቶች መጠገናቸው ተገልጿል።

Äthiopien I West Wollega - Gimbi Stadt
ምስል Negassa Dessalegn/DW

የቶሌ ተፈናቃዮች ዳግም ለመመለስ ዋስትና ይሻሉ

This browser does not support the audio element.

ከምዕራብ ወለጋ ዞን  ሶስት ወረዳዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀያቸው ለመመለስ የወደሙ ቤቶችን መልሶ መገንባቱን የዞኑ ቡሳ ጎኖፋ/የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ በተለይም በዞኑ  በሰኔ 2014 ዓ.ም  ከጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ ዜጎችን በመጀመሪያ ዙር ለመመለስ 60 ያህል የወደሙ ቤቶች መጠገናቸውን የዞኑ ቡሳ ጎኖፋ/አደጋ ስጋት ስራ አመራት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ነጸነት አለማየሁ አስረድተዋል፡፡ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ በአካባቢው የተሰሩ መልሶ ግንባታ ስራዎችን ከተፈናቀሉ ዜጎች የተወከሉና የመንግስት አመራሮች ቦታው ድረስ ሄደው ምልከታ ስለማድረጋቸውም ጠቁሟል፡፡ በቶሌ ከ221 አባወራዎች እንደሚመለሱም ተናግረዋል፡፡በምዕራብ ወለጋ ዞን 338 ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ

 በምዕራብ ወለጋ ዞን ከጉልሶ፣ባቦ ጋምቤልና ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ ዜጎችን በዚህ በዓመት ወደ ቀድሞ ቀያአቸው ለመመለስ የወደሙ መሠረተ ልማቶች እየተጠገኑ ስለመሆኑ የዞኑ ቡሳ  ጎኖፋ/አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ነጻነት አለማየሁ በሰኔ 11/2014 ዓ.ም በዞኑ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ተከስቶ በነበረው የጸጽጣ ችግር የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ ዝግጅት መደረጉን ጠቁሟል፡፡ በቶሌ ቀበሌ ተፈናቅለው ከነበሩት 1355 ሰዎች ለመመለስ  የተቃጠሉ ቤቶች መጠገናቸውን ገልጸዋል፡፡

 በምዕራብ ወለጋ ዞን ከጉልሶ፣ባቦ ጋምቤልና ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ ዜጎችን በዚህ በዓመት ወደ ቀድሞ ቀያአቸው ለመመለስ የወደሙ መሠረተ ልማቶች እየተጠገኑ ስለመሆኑ የዞኑ ቡሳ  ጎኖፋ/አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ምስል Negassa Dessalegn/DW

‹‹በሰላም እጦት የተፈናቀሉትን ለመመለስ አቅደናል፡፡ ከሶስት ወረዳዎች የጠፈናቀሉ ዜጎችን  ለመመለስ እየሰራን ነው፡፡ አንደኛው ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ባቦ ጋምልቤ እና ጉልሶ ወረዳ ናቸው፡፡ 601 አባወራዎችን በመጀመሪያ ዙር ለመመለስ አቅደናል፡፡ በቅድሚያ የሚገቡት ከቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ ሲሆን 60 ቤቶችን ጠግነናል፡፡ ከቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉና የተመዘገቡ 221 አበዎራዎች ባጠቃላይ 1355 ሰዎች ለመመለስ ቅድሜ ዝግጅት አጠናቀናል፡፡ ለሚመለሱ ዜጎችም  አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ተሟልተዋል፡፡‹‹

ወደ አካባቢው የመመለስ ፍላጎት የለንም

ሰኔ 11/2014 ዓ.ም ከግምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ጃራ መጠለያ እንደሚገኙ የነገሩን አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉን ነዋሪም በአካባቢው አሁንም ስጋት መኖሩን በመግለጽ ወደ ቦታው ለመመለስ ፍላጎት እንደለላቸው ጠቁሟል፡፡ በቅርቡ ወደ አካባቢው ሄደው የነበሩ የተፈናቀሉ ሰዎች  ተመልሰው ወደ ደብረ ብርሀን ስለመሄዳቸው ጠቁመዋል፡፡ምዕራብ ወለጋ ውስጥ የተፈናቀሉት መመለሳቸው

ሌላው ከቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ በወሎ አርቡ የሚባል ቦታ እንደሚገኙ የነገሩን ነዋሪ ወደ አካባቢው መመለስ እንዲፈልጉ እና በስፍራው ለወደመባቸው ንብረት ካሳ እንዲሰጣቸው እንዲሁም የድርጊቱ  ፈጻሚዎች ለህግ መቅረብ እንዳለባቸው ይገልጻሉ፡፡ በቀበሌው መኖሪያ ቤታቸውን ጨምሮ የነበራቸው ንብረት ሙሉ በሙሉ እንደወደመባቸው ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም በደረሰው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሐን ዜጎች ህይወት ማለፉ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ 6 በሚደርሱ መንደሮች ላይ ደርሷል በተባለው ጥቃት ከ4 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውም ተገልጾ ነበር፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW