ከሮም መጠለያ የተሰወሩ ስደተኞች 16 ኅዳር 2006ሰኞ፣ ኅዳር 16 2006ባለፈው ጥቅምት ወር በኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ ከምስራቅ አፍሪቃ የመጡ ከ500 በላይ ስደተኞችን ያጨቀች ጀልባ ላይ እሳት ተነስቶ በርካቶች ባህር ሰምጠዉ መሞታቸዉ ይታወሳል።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግምስል AFP/Getty Imagesማስታወቂያ በዚህ አደጋ የ360 ስደተኞች ህይወት ጠፍቷል። ከአደጋው ከተረፉት ስደተኞች 89ኙ ከላምፔዱዛ ወደ ሮም የተዛወሩ ሲሆኑ ስደተኞቹ ከተጠለሉበት የሮሙ የስደተኞች ማዕከል መጥፋታቸው ነው የተነገረው። የሮም ዘጋቢያችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ወደ ስደተኞቹ መጠለያ ጣቢያ ተጉዞ ስለጠፉት ስደተኞች ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ልደት አበበ ሂሩት መለሰ